የክርስቲን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት (CCRDA) ከ50 ዓመታት በላይ በልማትና በጎ አድራጎት ሥራ ላይ በማገልገል ላይ የሚገኝ ሲሆን ድርጅቱ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Consortium of Christian Relief and Development Association (CCRDA) (የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት)
የጨረታ ማስታወቂያ 01/2019
የክርስቲን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት (CCRDA) ከ50 ዓመታት በላይ በልማትና በጎ አድራጎት ሥራ ላይ በማገልገል ላይ የሚገኝ ሲሆን ድርጅቱ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታውን መመሪያ እና ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ እየከፈሉ አዲስ አበባ ከተማ ቃሊቲ የመንገድ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎችና ሜካኒኮች ማሰልጠኛ ፊትለፊት በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ማስታወቂያው በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ መግዛትና ተሽከርካሪዎቹን ባሉበት ሁኔታ ማየት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት (CCRDA) ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከኦርጂናሉ የመጫረቻ ሰነድ ጋር እባሪ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ከሆነ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች ስለ ንብረት አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ የተቀመጠውን የተጫራቾች መመሪያ ማንበብ ይኖርባቸዋል፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0114 393393 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
