በደ/ኢ/ክ/መንግሥት በጌዴኦ ዞን የዲላ ወ/ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለዲላ ዙሪያ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን ማለትም ሎት 1/ የጽሕፈት መሣሪያ ዕቃ ግዥ ሎት2/ የሞተር ሳይክል ግዥ ሎት 3/ የደንብ ልብስ ግዥ ሎት 4/ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ እና ሎት 5/ የፈርኒቸር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የዲላ/ዙ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ዋና/የሥራ ሂደት
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 001/2019ዓ.ም
በደ/ኢ/ክ/መንግሥት በጌዴኦ ዞን የዲላ ወ/ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለዲላ ዙሪያ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን ማለትም ሎት 1/ የጽሕፈት መሣሪያ ዕቃ ግዥ ሎት2/ የሞተር ሳይክል ግዥ ሎት 3/ የደንብ ልብስ ግዥ ሎት 4/ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ እና ሎት 5/ የፈርኒቸር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው
- የ ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
ከላይ በዝርዝር የተቀመጠውን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 በመክፈል ከዲላ ዙ/ወ/ ገቢዎች ጽ/ቤት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ ስለሆነም ተጫራቾች ማሟላት ያለበት መስፈርት
- ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት 5000/አምስት ሽህ ብር/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ሆኖ በጥሬ ገንዘብ ዋስትና ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ዕቃ የሚሸጡበትን ዋጋ በተዘጋጀው ዝርዝር ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው አንድ ኦርጂናል ሰነድ እና ሁለት ኮፒ ሰነድ በተለያየ ፖስታ ካሸጉ በኋላ ከሲፒኦ ጋር በአንድ ትልቅ ፖስታ በሰም በማሸግ ማቅረብ የሚችል፡፡
- በኦርጂናልና በኮፒ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ በሚታይ መልኩ በድጋሚ ተጽፎ በተጫራች /በሕጋዊ ተወካይ/ መፈረም አለበት፡፡
- በእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ ላይ ሕጋዊ የድርጅት ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች/ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ነገር ግን የ16ተኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሳጥን የሚገኘው በዲላ/ዙ/ወ/ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ግዥና ንብ/አስ/ዋና/የሥራ ሂደት ነው፡፡
- በጨረታ ተወዳድረው ያሸነፉበትን ዕቃዎች በዲላ/ዙ/ወ/ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ የማጓጓዝ የማስጫን እና የማውረጃ ወጭ ችለው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ የሆነ ተጫራች ለጽሕፈት መሣሪያ ዕቃ እና ለደንብ ልብስ ግዥ ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ላይ መገኘት/ አለመገኘት የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉልም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0970904657/0976086019
የዲላ/ዙ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ዋና/የሥራ ሂደት
✨ messages.ai_summary
Dilla Zuria Woreda Finance & Plan Office seeks suppliers for durable and consumable office goods in five lots: stationery, motorcycles, uniforms, electronics, and furniture. Bidders must submit a renewed business license, commercial registration, supplier registration, TIN, and VAT registration.
