Tender Detail

Tender Details

  • Company በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 ጤና ጣቢያ
  • Address ጀሞ ሚካኤል (አፍሪካ ሕንፃ ) ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-84 -40-316
  • Website
  • Deadline30 Oct 2026, 5:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceበየሎቱ ብር 300.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityበየሎቱ ከብር 2,000 እስከ 30,500 (CPO)
  • opening dateበ11ኛው ቀን 4፡00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Pharmaceutical Products , Stationery Materials

ደንብ ልብስ፣ የፅዳትና የቢሮ እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ መድሃኒትና ሪኤጀንት፣ ጥገና፣ ትራንስፖርት፣ ህትመትና ባዮሜዲካል ጥገና ግዥ (9 ሎቶች, 001/2019) - የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 ጤና ጣቢያ


የአንደኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 001/2019

በን/ስ/ላ/ክ/ከ የወረዳ 02 ጤና ጣቢያ የ2019 ዓ.ም በጀት አመት የሚፈልጋቸውን፡

  • ሎት 1 ደንብ ልብስ---10,000.00
  • ሎት 2 አላቂ የፅዳት እቃዎች--10,000.00
  • ሎት 3 አላቂ የቢሮ እቃዎች -12,000.00
  • ሎት4 ቋሚ እቃዎች -16,000.00
  • ሎት 5 መድሃኒት እና የላብራቶሪ ሪኤጀንት----30,500.00
  • ሎት 6 የጥገና እቃዎች -5,000.00
  • ሎት7 ትራንስፖርት - -2,000.00
  • ሎት 8 ህትመት -5,500.00
  • ሎት 9 የባዮ ሜዲካል የጥገና መሳሪያዎች--5,000.00

ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል በዚህ መሰረት ፡-

  1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው, ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በመንግስት ግዥ ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ የተመዘገቡ ፤ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. ተጫራቾች የጨረታው ለእያንዳንዱ ሎት ለሚወዳደሩበት ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ ከላይ በሎት የተሰጡትን ማስከበሪያ ብር ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
  3. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን በጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በየሎቱ በመክፈል በን/ስ/ላ/ክ/ከ የወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ጀሞ ሚካኤል (አፍሪካ ህንፃ) ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሮ ቁጥር 50 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በፋይናንስ ግዥ ቢሮ ቁጥር 50 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10ኛው ቀን (በአስረኛው ቀን ) 11፡30 /አስራ አንድ ተኩል / ይታሸጋል፤ በ11ኛው ቀን በቢሮ ቁጥር 50 አራት ሰዓት(4፡00) ይከፈታል፤ የመክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጠለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለሌሎች በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሰረት ማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ከቫት ጋር ያለውን ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል ፤
  8. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፤ ተጫራቾች 10% የውል ማስከበርያ በማስያዝ ውል ይፈጽማል ፡፡
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚ መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ
አድራሻ ፡- በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ጣቢያ ጀሞ ሚካኤል (አፍሪካ ህንፃ ) ፊት ለፊት ይገኛል፡፡
ስልክ ቁጥር 0972705152

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ

✨ messages.ai_summary
Procurement of uniforms, cleaning and office supplies, fixed assets, medicines and lab reagents, maintenance items, transport, printing, and biomedical maintenance equipment, split into 9 lots. Eligible bidders must have a renewed business license, tax compliance, supplier registration, TIN/VAT, and submit samples per lot.
Save Tender