Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፔፕሲ ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የሐዋሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት አዲሱ የውርስ መጋዘን ቅጥር ግቢ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462125896
  • Website
  • Deadline23 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 100 (የማይመለስ, ኦንላይን)
  • Bid Securityየሚጫረቱበት ዋጋ 5% (CPO)
  • opening dateኦንላይን (አክሽን ኢትዮጵያ)
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

የተተዉና የተወረሱ ዕቃዎች (መገናኛ፣ አልባሳት፣ ኤሌክትሪክ፣ መዋቢያ፣ ምግብ ነክ፣ የመኪናና ሞተር መለዋወጫ) ሽያጭ (12/2019, በአክሽን ኢትዮጵያ) - የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት

በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር- 12/2019
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ

የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 4(1) መሠረት የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የመዋቢያና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች የቤትና ቢሮ ዕቃዎች የተለያዩ የምግብ ነክ ዕቃዎች የመኪና እና የሞተር ሳይክል አካላትና መለዋወጫ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች(ግለሰብም ሆነ ድርጅት) ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎች ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ስካን በማድረግ ኦንላይን የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርቦታል።
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው ጊዜ መሰረት በማንኛውም ጊዜና ሰዓት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ኦንላይን በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  3. ያገለገለ ተሽከርካሪ/ሞተርሳይክል) ላይ መወዳደር የሚፈልግ ተጫራች ማንኛውም እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ መወዳደር ይችላል፡፡
  4. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥም የተዘጋጀ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን C.P.O በማሰራት ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. ቅ/ጽ/ቤቱ ቢሮ ወይም ወደ አክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በአካል በማስያዝ ወይም በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  5. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ላይ ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው ቀን ጥቅምት 08 ቀን 2019 ጀምሮ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን ሂደት በኦንላይን መከታተል ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታዉ ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ዉጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ዉድድር ማግለል አይችልም። በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በሶስት (3) ቀናት የሚመለስላቸው ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ሳያዩ በተለጠፈው ፎቶ ብቻ ተመልክተው ለሚሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  11. ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ እና በተለየው ኮድ ነው፡፡
  12. አሸናፊው ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ዕቃው ድጋሚ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል፡፡
  13. ቅ/ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ በመመዝገብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ 09-05-11-55-11 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን ሥራ ሂደት የስልክ ቁጥር 046-212-53-96/046- 212-65-95 ይደውሉ
የቴሌግራም ግሩፕ -https://t.me/hawassaawegaged (ECCH-አወጋገድ ሥራ ሂደት 2018) ይጠቀሙ

የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Hawassa Customs Office is selling abandoned and confiscated goods by open bid via the Auction Ethiopia platform, including communications equipment, clothing, electrical goods, cosmetics, food items, and vehicle/motorcycle parts. Bidders (individuals or firms) need a renewed trade licence, VAT registration, TIN and proof of tax payment. Importers/owners and their families may not bid.
Save Tender