Tender Detail

Tender Details

  • Company የአርባ ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ
  • Address በአ/ምንጭ ሁለገብ ስታዲየም የክለብ ጽ/ቤቱ ይገኛል። አርባምንጭ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-8-81-36-05
  • Website
  • Deadline26 Oct 2026, 3:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 300.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityለእያንዳንዱ ጨረታ ብር 10,000.00 (CPO)
  • opening dateበዕለቱ 9፡30
  • Categories Sport Materials And Sportswear

የአ/ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በ2019 ዓ.ም የውድድር ዘመን የስፖርት ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊውን በመለየት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የአርባ ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ


የጨረታ ማስታወቂያ

የአ/ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በ2019 ዓ.ም የውድድር ዘመን የስፖርት ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊውን በመለየት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ማሟላት የሚትችሉ ተወዳዳሪዎች እንድትሳተፉ እንጋብዛለን፡-

  1. በየዘርፉ የተሰማራበት ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ ፣ የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰና የዘመኑን ግብር የከፈለ ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ጨረታ 10,000.00 /አስር ሽህ ብር/ በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችል፡፡
  3. አሸናፊ ድርጅት ለመልካም የሥራ አፈፃፀም የምስክር ወረቀት/ማስረጃ ማቅረብ የሚችልና የጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ ማስያዝ የሚችል፡፡
  4. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ በአ/ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን እንዲገዙ እየገለጽን እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ መግለጫውን በማያሻማ መልኩ እና ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በመሙላት ሁሉም የጨረታ ሰነዶች ኦርጅናልና ኮፒ በድምሩ 2 ፖስታዎች በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከፊትና ጀርባው ላይ የድርጅቱን ማህተምና የባለቤትነት ፊርማ በማድረግ በእናት ፖስታ ውስጥ ተጨምሮ ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ቅዳሜና እሁድን የማያካትት ይሆናል፡፡
  5. የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ ማቅረብ የሚችል፡፡
  6. በጨረታው ያሸነፈ ተወዳዳሪ የባለሙያ አስተያየት ላይ መሠረት በማድረግ ውል ገብተው ወደ ስራ የሚገባ ይሆናል፡፡ ሁሉም ተጫራች አድራሻውንና ቦታውን እንዲሁም የስልክ ቁጥር መግለጽ ይኖርበታል፡፡በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
  7. የእያንዳንዱ ግዥ መጠን በሽያጭ ሠነዱ ላይ በተገለፀው መሠረት ሃያ በመቶ ሊጨምርም ሆነ ሊቀንስ ይችላል፡፡
  8. መ/ቤቱ የዕቃው ጥራት በባለሙያና በስፖርተኞች ሲረጋገጥ ብቻ ውል ተዋውሎ ማስቀጠል የሚቻል ይሆናል፡፡
  9. በጨረታው ማስታወቂያው ላይ ያልተገለጹ ተጨማሪ ማሳሰቢያዎች በጨረታ ሠነዱ ላይ የሚገለጹ ካሉ እንደ ማስታወቂያ የሚያገለግል ስለሆነ ሁሉም ተጫራች ትኩረት ሊሰጥበት ይገባል፡፡
  10. ክለብ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በ6ኛው ቀን ሲሆን በዕለቱ 9፡00 ሰአት የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸግ ሆኖ በዕለቱ 9፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የማይገኙ ከሆነ የጽ/ቤቱን ስራ አያስተጓጉልም፡፡ የተጫራቹ ተወካይ የሚቀርብ ከሆነ ስለ ውክልናው ህጋዊነት የሚገልጽ መረጃ ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  12. የክለብ ጽ/ቤቱ አድራሻ በአ/ምንጭ ሁለገብ ስታዲየም የሚገኝ ሲሆን

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0900988962 (0916876722) ይደውሉ፡፡

የአርባ ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ

✨ messages.ai_summary
Arba Minch City Football Club seeks bidders to supply sports materials for the 2019 season via open tender. Eligible bidders must hold a valid business license, be VAT-registered, and provide a registration certificate. The winning firm must submit a performance certificate and a 10% performance bond.
Save Tender