Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዋሽ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Address , Phone: 09-13-97-49-27
  • Website
  • Deadline30 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityግልጽ ጨረታ፡ የእቃ ኮድ 5%፤ ሐራጅ፡ ብር 100,000 (CPO)
  • opening dateሐራጅ፡ 20/02/2019 ዓ/ም 5፡00 ሰዓት
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በ20/02/2019 ዓ/ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ በአክሽን ኢትዮጵያ(auction ethiopia) መተግበሪያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የአዋሽ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በ20/02/2019 ዓ/ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ በአክሽን ኢትዮጵያ(auction ethiopia) መተግበሪያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች መተግበሪያውን ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር auction Ethiopia ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ በመመዝገብና የጨረታ ሰነዱን በማየት፣ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን፣ የእቃዎችን ሳምፕል ከአክሽን ኢትዮጵያ ድረ-ገጽ(auction ethiopia page) ወይም አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በቴሌግራም እንዲላክሎዎት በማድረግ ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የጨረታ መስፈርቶች-

  1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ ከሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለ መሆኑ ክሊራንስ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በሲስተም አታች ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 20/02/2019 ዓ/ም ከአክሽን ኢትዮጵያ ድረ-ገጽ(auction ethiopia page) ማየት ይችላሉ፡፡
  3. ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በማስያዝ በሲስተም አታች ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
ተ.ቁ አጫራች ቅ/ጽ/ቤት የጨረታው ዓይነት ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት
1 አዋሽ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ ጫማዎች፣ አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የሞባይል ቀፎና አክሰሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ምግብ ነክ ፣የስፖርት እቃዎች፣የእጅ ሰዓት፣ ኮስሞቲክስ፣መነፅር እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች ለግልጽና ለሐራጅ ጨረታ በ20/02/2019 እስከ ጠዋቱ 3፡45 ለግልጽ ጨረታ መዝጊያ ጊዜ በ20/02/2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ በ20/02/2019 ዓ/ም 5፡00 ሰዓት ይሆናል ፡፡
  • 4. የጨረታው መክፈቻ ሰዓት እና ቀንን ከአክሽን ኢትዮጵያ ድረ-ገጽ(auction ethiopia page) በማየት የጨረታው ሂደት ተጀምሮ ከማለቁ በፊት ዋጋ መስጠት ይችላሉ፡፡
  • 5. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (c.p.o) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  • 6. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዘን ማውጣት ይኖርበታል፡፡
  • 7. ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
  • 8. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • 9. የአክሽን ኢትዮጵያ(auction othiopia) መተግበሪያን በተመለከተ የጥሪ ማእከሉን ሠራተኛ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 09-05-11-55-11/011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • 10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-13-97-49-27 ይደውሉ፡፡

የአዋሽ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Awash Customs Branch invites bidders to buy various confiscated contraband goods (shoes, clothing, car spare parts, mobile cases/accessories, electronics, food items, sports goods, watches, cosmetics, eyeglasses and other items) via open and auction sale on the Auction Ethiopia app. Bidders need a renewed trade license, VAT registration, tax clearance and VAT activity certificate.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender