Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ጅግጅጋ ከተማ ፡ ሶማሌ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0913220473
  • Website
  • Deadline22 Oct 2026, 9:45 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityሀራጅ፡ ብር 500,000 CPO፤ ግልፅ ጨረታ፡ የመጫረቻ ዋጋ 5% CPO
  • opening dateግልፅ ጨረታ 12/02/2019 4፡00፤ ሀራጅ 4፡15
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

በኮንትሮባንድ የተያዙ አልባሳት፣ ኮንስትራክሽን፣ የቤት እቃ፣ ጫማ፣ ምግብ ነክ፣ ስፔርፓርትና ልዩ ልዩ እቃዎች የግልፅና የሀራጅ ሽያጭ - የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት

በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


የግልፅ እና የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ አልባሳት፣ ኮንስትራክሽን፣ የቤት እቃ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ ጫማዎች፣ ምግብ ነክ፣ ስፔርፓርት፣ የጽዳት እቃ እና ልዩ ልዩ በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች በቀን 10/02/2019 ጀምሮ ሳምንቱ በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልጻል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች ፦

  1. በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ በመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የቀረበለት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤
  2. ለሀራጅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ማቅረብ የሚችል፤
  3. ለግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማቅረብ የሚችል፤
  4. ለሀራጅ ጨረታ ተጫራቹ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ በራሱ ያቀርባል፤
  5. ለግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፤
  6. ተጫራቹ በጨረታው አሸናፊ የሆነውን እቃዎች ወዲያውኑ ክፍሎ በ05 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆን አለበት፤
  7. እቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤
  8. በጨረታው ያልተሳኩ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤
  9. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካለገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይቻላል፤
  10. ማንኛውም ተጫራች እቃዎቹን ከሸጠ በኋላ ከጅግጂጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየሁኔታው እርቀት በቀን ገደብ መሸኛ ሊሰጠው ይችላል፤
  11. ተጫራቾች እቃዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የተገኘ እቃ ቢያዝ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፤
  12. ተጫራቾች የምትሞሉትን ግልጽ ጨረታ ሰነድ ከቀን 10/02/2019 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የዕቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በቀን 12/02/2019 3፡45 ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤
  13. የሀራጅ ጨረታው የሚካሄደው በቀን 12/02/2019 ከረፋዱ 4፡15 በቅ/ጽ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤

N.B፦ አሸናፊው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ለምግብ ነክ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Jigjiga Customs Office invites eligible bidders to buy confiscated clothing, construction materials, furniture, footwear, food items, spare parts, cleaning supplies and other goods via open and auction sale. Bidders need a valid trade licence, TIN, VAT certificate and tax payment proof.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender