Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Address አዳማ በከልቻ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር አጠገብ ያለው ቢሮአችን ሦስተኛ (3) ፎቅ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 022-211-58-07
  • Website
  • Deadline20 Oct 2026, 4:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 100 (በአክሽን ኢትዮጵያ)
  • Bid Securityበየምድቡ (ከብር 500 እስከ 3,915,400.00) CPO በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
  • opening date10/2/2019 ዓ.ም 10፡00
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

የተወረሱ አልባሳት፣ ሸቀጣሸቀጥ፣ ኮስሞቲክስ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የኮንስትራክሽን ማቴሪያል፣ መለዋወጫና ሞተር ሳይክሎች የሐራጅ ሽያጭ (09/2019, በአክሽን ኢትዮጵያ) - የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት

የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ ሐራጅ ቁጥር 09/2019

በአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ሳይፈፀምባቸው የተወረሱ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ አዳዲስ አልባሳት (የመጋረጃ ጨርቆች፣ የሱፍ ጨርቆች) ሸቀጣሸቀጥ ልዩ ልዩ፣ኤሌክትሮኒክስ፣ ተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ ጎማዎች፣ ኮስሞቲክስ፣ የቢሮ መገልገያ እቃዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣አዳዲስ አልሳት፣ የኮንስትራክሽን ማቴሪያል፣ የኮንስትራክሽን ማቴሪያል (ቧንቧ እቃዎች) እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችን በሃራጅ ጨረታ በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-

  1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ አንቀሳቃሾችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በአክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም ግምታዊ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆነ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ ሰነዱን አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች አክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት መመልከት ይችላል፡፡
  4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚወጣበት ቀን እና የሚያበቃበት እንዲሁም ሰዓት ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ የተገለጸ ነው፡፡
ተ.ቁየእቃው አይነትየጨረታው አይነትበአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመበት ቀንጨረታው የሚካሄድበት ቀንጨረታው የሚጀምርበት ሰዓትጨረታው የሚከፈትበት ሰዓትስልክ ቁጥር
1አዳዲስ አልባሳት (የመጋረጃ ጨረቶች፣ የሱፍ ጨርቆች)ሃራጅ5/2/201910/2/20194፡0010፡000221118429/0222118925
2ሸቀጣሸቀጥ ልዩ ልዩሃራጅ5/2/201910/2/20194፡0010፡000221118429/0222118925
3ኮስሞቲክስሃራጅ5/2/201910/2/20194፡0010፡000221118429/0222118925
4የኮንስትራክሽን ማቴሪያልሃራጅ5/2/201910/2/20194፡0010፡000221118429/0222118925
5የኮንስትራክሽን ማቴሪያል (ቧንቧ እቃዎች)ሃራጅ5/2/201910/2/20194፡0010፡000221118429/0222118925
6ኤሌክትሮኒክስሃራጅ05/2/201910/2/20194፡0010፡000221118429/0222118925
7አዳዲስ አልባሳትሃራጅ05/2/201910/2/20194፡0010፡000221118429/0222118925
8የተሽከርካሪ መለዋወጫሃራጅ05/2/201910/2/20194፡0010፡000221118429/0222118925
9የቢሮ መገልገያ እቃዎችሃራጅ5/2/201910/2/20194፡0010፡000221118429/0222118925
10ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችሃራጅ5/2/201910/2/20194፡0010፡000221118429/0222118925

በጨረታው ሽያጭ የእቃዎቹ አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የሆነ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም፡፡

በሃራጅ ጨረታ ለምትወዳደሩ ለጨረታው ዋስትና የሚሆን ማለትም፤ ለምድብ 1 የመጋረጃ ጨርቅ 3,915,400.00፣ ለምድብ 2 የሱፍ ጨርቅ 1,880,000.00፣ ለምድብ 3 የሱፍ ጨርቅ 2,410,100.00፣ ለምድብ 4 ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) 33,300.00 ብር፣ ለምድብ 5 ኮስሞቲክስ 406,400.00 ብር፣ ለምድብ 6 የኮንስትራክሽን ማቴሪያል 213,500.00 ብር፣ ለምድብ 7 ኮስሞቲክስ 849,300.00 ብር፣ ለምድብ 8 ኮስሞቲክስ 204,500.00 ብር፣ ለምድብ 9 የኮንስትራክሽን ማቴሪያል(ቧንቧ እቃዎች) 219,400.00 ብር፣ ለምድብ 10 ኤሌክትሮኒክስ 119,100.00 ብር፣ ለምድብ 11 ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) 127,100.00 ብር፣ ለምድብ 12 ኮስሞቲክስ 15,000.00 ብር ፤ ለምድብ 13 አዳዲስ አልባሳት 37,300.00 ብር፣ ለምድብ 14 ኮስሞቲክስ 2,500.00 ብር፣ ለምድብ 15 ኤሌክትሮኒክስ 44,500 ብር፣ ለምድብ 16 ኤሌክትሮኒክስ 60,300.00፣ ለምድብ 17 ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) 4,100.00 ብር፣ ለምድብ 18 ተሽከርካሪ መለዋወጫ 500 ብር፣ ለምድብ 19 ጎማዎች 4,100፣ለምድብ 20 ተሽከርካሪ መለዋወጫ 61,600.00 ብር፣ ለምድብ 21 ተሽከርካሪ መለዋወጫ 17,200.00 ብር፣ ለምድብ 22 የቢሮ መገልገያ እቃዎች 1,800.00 ብር፣ ለምድብ 23 የቢሮ መገልገያ እቃዎች 2,300.00 ብር፣ ለምድብ 24 የኮንስትራክሽን ማቴሪያል(Plastic tile spacers) 250,600.00 ብር እና ለምድብ 25 ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች 25,000.00 ብር በ (Customs Adama Branch) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ በማሰራት ያሰሩትንም ሲ..ፒ.ኦ. በአካል ወደ አክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡

በሃራጅ ጨረታ ለመሸጥ የወጡትን እቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 ውስጥ እንዲሁም ብዛቱ 556 ፓኬድ አዳዲስ አልባሳት (የሱፍ ጨርቆች) በአዳማ ቆርቆሮ መ/ቤቱ አዲስ በተከራየው መጋዘን ቁጥር 5 የሚገኝ ሲሆን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ማየት እና መጫረት ይቻላል፡፡

በሐራጅ ጨረታ እቃዎቹ የመነሻ ዋጋ ያልተወሰነላቸው ስለሆነ የመነሻ ዋጋ በተጫራች የሚሰጥ ይሆናል፡፡

  • አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን፤ ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 /ሶስት የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  • አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን ... ይኖርባቸዋል፡፡
  • ከላይ በተ/ቁ 10 ላይ በተገለፀት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ... ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
  • ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እ... አይችሉም፡፡
  • ቅ/ጽ/ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠቀ ነው፡፡
  • ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን፡፡

NB:- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን መረጃዎች ያላሟሉ ተጫራቾች ቢያሸንፉ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዙትን ሲፒኦ ለመንግስት ገቢ በማድረግ እቃው በድጋሜ ጨረታ የሚወጣ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

➢ የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-5511/ 011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ፡- አዳማ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን የስራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች 0221118429 እና 0222118925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Adama Customs Branch is auctioning confiscated goods via the Auction Ethiopia app only: clothing, textiles, general goods, cosmetics, electronics, construction materials, vehicle spare parts, tires, office supplies, and used motorcycles. Bidders need a renewed trade license, VAT registration, and tax clearance; VAT registration is waived for items under 500,000 birr. Importers or owners cannot participate.
Save Tender