Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline02 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100(አንድ መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 30000.00(ሰላሳ ሺህ) ብር በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ
  • opening dateበዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ባለቤት ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን ይከፈታል። እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
  • Categories Cleaning & Janitorial , Textile, Garment & Leather , Stationery Materials

በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በ2019 የበጀት ዓመት ለፍርድ ቤታችን የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ አላቂ እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች እና ኤልክትሮኒክስ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ

በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በ2019 የበጀት ዓመት ለፍርድ ቤታችን የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ አላቂ እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች እና ኤልክትሮኒክስ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ፣ ከዚህ በታች የተገለፀውን መመሪያ በመከተልና ከዚህ ጋር ተያይዞ በቀረበው እስፔስፍኬሽን መሰረት ተጫራቾች ይህንን ጨረታ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።

  1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ኪሊራንስ ማቅረብየሚችሉ።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒውን ለብቻ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ሰነዱን ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 100 /አንድመቶ/ ብር ከሱሉልታ ክፍለከተማ ፍርድ ቤት መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 30000.00(ሰላሳ ሺህ) ብር በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል ።
  5. ጨረታው በ21ኛው የስራ ቀን 4:00 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ባለቤት ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን ይከፈታል። እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች ሙሉ ሰነዶቻቸው፣ ሥማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።
  7. ተጫራቾች የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ የተጻፈ መሆን አለበት።
  8. ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ጨረታው ላይ ሲቀርብ (ለመሳተፍ) ሙሉ የኦዲት ርፖርት የ2018 ዓ.ም መቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  9. ተጫራቾች የምትወዳደሩበት የእቃው አይነት ላይ ሳምፕል (sample) መቅረብ ይኖርበታል። ምክንያቱም የምትወዳደሩት ባቀረባችሁ sample ስለሆነ፣ Sample የደንብ ልብስ፣ እስቴሽነሪ፣ የፅደት ቋሚ እና አላቂ ሲሆን ኤልክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር በፎቶ መቅረብ ይኖርባቸዋል።
  10. ግዥው ከ 20000.00 ብር በላይ ከሆነ 50% ቫት ጽ/ ቤቱ ይቆረጣል።
  11. በጨረታው የተሸነፉትም ተሸናፊነታቸው እንደተረጋገጠ ለጨረታ ማስከበሪያ በዋስትና ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  12. ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ የመቆያ ግዜ (Price validity date) ከጨረታው መከፈቻ እለት ጀምሮ የሚጸናበትን ጊዜና ስራውን አጠናቆ የሚያስረክብበትን ጊዜ(Delivery time) መግለጽ ይኖርባቸዋል።
  13. አሸናፍዎች እቃው እስከ መስሪያቤቱ ድረስ መቅረብ ይኖርባቸዋል።
  14. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት
የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት

✨ messages.ai_summary
Sululta Sub-city Woreda Court invites bids for stationery, cleaning supplies, furniture, consumables, uniforms, and electronics. Bidders need a valid trade license, tax clearance, and must submit samples (photos for electronics/furniture). MSEs must provide a full 2018 audit report.
Save Tender