Tender Detail

Tender Details

  • Company በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት
  • Address በጋሞ ዞን አርባምንጭ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-181-40-91
  • Website
  • Deadline03 Nov 2026, 11:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 100 (የማይመለስ)
  • Bid Securityለእያንዳንዱ ሎት ብር 20,000 (በጥሬ ገንዘብ ወይም CPO)
  • opening dateበዕለቱ 8፡00 ሰዓት
  • Categories Transportation Service And Cargo , Construction Materials And Raw Materials , Vehicle Spare Parts

የአፈር ማዳበሪያ ማጓጓዣ አገልግሎት፣ የሕንፃ መሳሪያዎች፣ ቀለምና የመኪና መለዋወጫ ግዥ (4 ሎቶች) - ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት

በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት የተለያዩ የግዥ አገልግሎቶችን

  • ሎት-1 የአፈር ማዳበሪያ ከዞን ማዕከል ወደ ቀበሌያትና ከቀበሌያት ወደ ቀበሌያት የማጓጓዣ አገልግሎት ግዥ፤-
  • ሎት-2 የሕንፃ መሳሪያዎች የፋብሪካ ውጤቶች ግዥ
  • ሎት-3 የታሸገ የቀለም ግዥ
  • ሎት-4 የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎችን

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡-

በዚሁ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የሚትፈልጉ በዘርፉ የተሰማራችሁ ድርጅቶችና ግለሰቦች ለጨረታው ውድድር ማቅረብ ያለባችሁ መስፈርቶች የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፤ የንግድ ስራ ምዝገባ ሰርትፊኬት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፊኬት፤የግብር መከፊያ ቁጥር የአቅራቢነት ሰርትፍኬትና የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻው ብር 20,000 /ሃያ ሺህ/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ክፍያ ማዘዣ CPO ከታወቀ ባንክ በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከመ/ቤቱ ግዥና ንብረት አስተዳዳር ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ የማይመለስ 100 /አንድ መቶ/ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ዋጋው ያለ ስርዝ ድልዝ በጥንቃቄ በመሙላት በሰነዱ ላይ ፊርማና ማህተም በማድረግ በፖስታ አሽጎ በፖስታው ላይም ማህተም የጨረታውን ዓይነት እና ስልክ በመጻፍ በዕለቱ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዕለቱ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን ድንገት የሥራ ቀን ሳይሆን ቢቀር በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ሂደቱ ይከናወናል፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፤- ከመዲኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ዝቅ ብሎ ወደ የትነበርሽ ማዞሪያ ላይ ባለው ዲንጉዛ ሕንፃ ውስጥ እንገኛለን፡፡

አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Procurement of soil fertilizer transport from zone center to kebeles and between kebeles, building materials, sealed paint, and vehicle spare parts, in four lots. Open to licensed firms and individuals in the sector. Required: renewed business license, commercial registration, VAT registration, TIN, supplier certificate, and bid security per lot.
Save Tender