Tender Detail

Tender Details

  • Company Awash Bank S.C (አዋሽ ባንክ አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115571107
  • Websitehttps://awashbank.com/am-et/
  • Deadline20 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 300.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityየመነሻ/የቀረበ ዋጋ ¼ኛ (CPO)
  • opening dateጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 4፡10 ሰዓት
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

ያገለገሉ 21 ተሽከርካሪዎች፣ 2 ሞተር ሳይክሎች እና የቢሮ መገልገያ ንብረቶች ሽያጭ ጨረታ - አዋሽ ባንክ አ.ማ.

Awash Bank S.C (አዋሽ ባንክ አ.ማ)


ያገለገሉ ንብረቶች የጨረታ ማስታወቂያ

አዋሽ ባንክ አ.ማ. ሲጠቀምባቸው የነበሩትን 21 ተሽከርካሪዎች እና 2 ሞተር ሣይክሎች በሎት (1) እና በሎት (2) (ጄኔሬተር" ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር" ፕሪንተር" ራክ ማውንት" ቼክ ስካነር" ስካነር" ሰርቨር" ዲሊንክ" የወረፋ መጠበቂያ" የብር መቁጠሪያ" የሣንቲም መቁጠሪያ" መፈተሻ" የሂሣብ መደመሪያ" የዶላር መፈተሻ ማሽን" ፋክስ" ፎቶ ኮፒ" የውሃ ማጣሪያ" ቴሌቭዥን" ላሚኔቲንግ (ዱዋል ID ፕሪንተር)" የሙቀት መለኪያ" ቬንትሌተር" ብሎወር" ቴፕ ሪከርደር" ዩቪ የብር መፈተሻ ማሽን" ኤክስቼንጅ ሬት ዲስፕሌይ ቦርድ" አየር ማቀዝቀዣ" ካሽ ቦክስ" ሪፍሪጄሬተር" እሳት ማጥፊያ" የተለያዩ ወንበሮች" ሶፋ" የተለያዩ የማስታወቂያ ምልክቶች" የተለያዩ ጠረጴዛዎች" የኮት መስቀያ" የመጽሐፍ መደርደሪያ" ካዝና" ፋይሊንግ ካቢኔት እና ላተራል ፋይሊንግ ካቢኔት) ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከታች የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚችል መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡-

  1. ስለ ጨረታው አፈጻጸም ዝርዝር መረጃ የማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ) በየትኛውም የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ በሂሣብ ቁጥር 01540000544500 በተጫራቹ ስም ገቢ በማድረግ ደረሰኙን አዋሽ ባንክ ባልቻ ሳፎ ሕንጻ 1ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል የቢሮ ቁጥር M-11 በመቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛትና ማስገባት ይችላሉ፤
  2. ተጫራቾች በሎት 1 ላይ ለተገለጹት ተሽከርካሪዎች በባንኩ የተቀመጠውን የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ኛ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) በአዋሽ ባንክ አክሲዮን ማህበር ስም አሰርቶ ማስገባት ይኖርበታል፤
  3. በሎት 2 ላይ ለተዘረዘሩት የቢሮ መገልገያ ንብረቶች ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ንብረት ያቀረቡትን ዋጋ ¼ኛ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) በአዋሽ ባንክ አክሲዮን ማህበር ስም አሠርቶ ማስገባት ይኖርበታል፤
  4. ያለ ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፤
  5. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) 15%፣ ለተሽከርካሪዎቹ የስም ማዘዋወሪያ፣ የተሽከርካሪ የዋጋ ግምት፣ በጨረታ ዋጋ እና የመንገድ ትራንስፖርት ባለሞያ ግምት መካከል ሊፈጠር የሚችለውን የተ.እ.ታ. የዋጋ ልዩነት ገዥ ይሸፍናል፤
  6. ንብረቶቹን አሸዋ ሜዳ በሚገኙት የባንኩ መጋዘኖች እንዲሁም ተሽከርካሪዎቹን በተመለከተ ልደታ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ባልቻ ሳፎ ሕንጻ በአካል ቀርበው እና የገዙትን የጨረታ ሰነድ በመያዝ በወጣው ፕሮግራም መሠረት መጐብኘት ይቻላል፤
  7. ጨረታው ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 4፡10 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባልቻ ሳፎ ሕንጻ 1ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል የቢሮ ቁጥር M-11 ውስጥ ይከፈታል፤ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈጽሞ ንብረቶቹን መረከብ ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ¼ኛ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ በማድረግ ጨረታው ይሰረዛል፤
  9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው"
  10. ስለ ጨረታው አፈጻጸም ዝርዝር ማብራሪያ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀን በፊት በስልክ ቁጥር 0115-303026/0115-303014 /0115-576815/ ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

አዋሽ ባንክ አ.ማ.

✨ messages.ai_summary
Awash Bank is selling used assets by bid: 21 vehicles and 2 motorcycles (Lot 1), plus assorted office equipment and furniture (Lot 2). Bidders must submit a CPO bid bond in Awash Bank S.C.'s name; bids without one are rejected. The winner covers 15% VAT and transfer costs.
Save Tender