ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የ2016 እና 2017 ሂሳብ ዘመን የሂሳብ ምርመራ (ኦዲት) ጨረታ - መሊቅ የስልጤ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን
መሊቅ የስልጤ ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሂሳብ ምርመራ ጨረታ
መሊቅ የስልጤ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ ማህበር የፋይናንሻል ሥራ እንቅስቃሴ ከጥቅምት 01/2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 30/2018 ዓ.ም ድረስ ያለውን የ2016 እና የ2017 ሂሳብ ዘመን የሁለት ዓመት ደጋፊ ሰነዶችን የያዘ የ2016 ዓ.ም. 39 እና የ2017 ዓ.ም. 49 ፋይል አቃፊ ሰነዶችን ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ኦዲት አድራጊው ተጫራቾች ማማላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-
- በኢትዮጵያ ሂሳባ አያያዝና ኦዲቲንግ ቦርድ ወይም እሱ ከሚወክለው አካል ሂሳብ ለመመርመር የሚያስ ችለው የሙያ ፍቃድ ያገኘ እና የሙያ ፍቃድ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤
- በሀገሪቱ ሕግ መሰረት የኦዲት ሥራን ለማከናወን የሚያስችል የዘመኑን ግብር የተገበረበት የታደሰ የንግድ ፍቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፤
- የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሂሳብ ምርመራን በተመለከተ ከፌዴራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ወይም ከሌሎች ሕጋዊ አካላት ሥልጠና የወሰደና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ቢሆን ይመረጣል፤
- ከሂሳብ መርማሪ ቡድን አባላት ውስጥ ቢያንስ አንዱ ከዚህ በፊት የኅብረት ሥራ ማህበራትን ሂሳብ የመ ረመረ ቢሆን ይመረጣል፤ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- በሂሳብ ምርመራ ያለውን የሥራ ልምድ አደራጅቶ ማቅረብ የሚችል፤
- የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሂሳብ ለመመርመር ብቁ ባለሞያዎችን በሥራ ላይ ማስማራት የሚችል ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚከሰተው ማንኛውም ኪሳራና ችግር አስቀድሞ ኃላፊነቱን መውሰድ የሚችል
- ሥራውን ለማጠናቀቅ የሚፈጀውን ጊዜና የአንድ ፋይል አቃፊ እና ጠ/ዋጋ ከነተጨማሪ እሴት ታክስ በመሙላት የሚያቀርብ፤
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አዲስ አበባ መርካቶ ከረሜላ ህንጻ 3ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 5 በሚገኘው የሥልጤ ልማት ማኅበር ጽ/ቤት በመቅ ረብ የተዘጋጀውን ሰንድ 200 ብር በመሊቅ የሥልጤ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒን በንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000085996278 አስገብቶ ሰነድ በመግዛት የሞሉትን ሰነድ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነዱን ለይቶ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ከላይ የተገለጹትና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በማያያዝና በፖስታ በማሸግ ማስገባት ይችላሉ፤
- የጨረታው ሳጥን በ15ኛው ቀን 08፡30 ታሽጎ በዚሁ ቀን 9፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተ ገኙበት የሚከፈት ሲሆን ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚፈጸም ይሆናል፤
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-
0920999940/0911978626/0945587862
አድራሻ፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ
መሊቅ የስልጤ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ ማኅበር
✨ messages.ai_summary
Melik Silte Farmers' Cooperative Union seeks audit of its 2016 and 2017 fiscal year financial activities, covering 39 and 49 file folders respectively. Bidders must hold a valid audit license from the Ethiopian Accounting and Auditing Board, a renewed business license and TIN, and preferably training from the Federal Cooperative Agency.
Not stated in the notice: bid security. Check the original document or ask the issuer.
