Tender Detail

Tender Details

  • Company Hagbes Pvt. Ltd. Company
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline31 Oct 2026, 12:00 PM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Priceብር 500.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityከዋጋው 10% (C.P.O.)
  • opening dateጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ/ም፣ ጠዋት 4፡30 ሰዓት
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች (ሎው ቤድ ተሳቢዎች፣ የጭነት መኪኖች፣ ፒክአፖችና ቀላል ተሽከርካሪዎች) እና የብረት የውሃ ማጠራቀሚያዎች ሽያጭ (ሐግ/ተሽጨ/02/2019) - ሐግቤስ ኃ/የተ/የግ/ማ

Hagbes Pvt. Ltd. Company


ሐግቤስ HAGBES
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችና የብረት የውሃ ማጠራቀሚያ ሽያጭ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡ ሐግ/ ተሽጨ/ 02/ 2019

ሐግቤስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከዚህ በታች የተገለፁትን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች አዲስ አበባ ከተማ ላይ ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተራ ቁጥርለጨረታ የቀረቡት ተሽከርካሪዎች ዓይነትብዛት
1ሎው ቤድ ተሳቢዎች ( low bed trailers)03
2ኪያ ሬይኖ የጭነት ተሽከርካሪ (KIA RHINO CARGO TRUCK) 50 ኩንታል02
3መጅረስ የጭነት ተሽከርካሪ (MAJRUS CARGO TRUCK)01
4ዴዉ ኖቨስ የውሃ ቦቴ (DAEWOO NOVUS WATER TANK)8000 ሊትር01
5ሞሶ ዴው ( MUSSO DAEWOO 4 seater)02
6ማህንድራ ቦሌሮ ፒክ አፕ(MAHINDRA pickup)02
7የብረት የውሃ ማጠራቀሚያ ( metal water tanker) 3000 ሊትር36
8የብረት የውሃ ማጠራቀሚያ ( metal water tanker) 2000 ሊትር87
9ቀላል ተሽከርካሪዎች ( ዴዉ ቲኮ፣ ሴይሎ፣ዳማስ (DAEWOO TCO, CIELO, DAMAS ) ኪያ ስፖርቴጅ፣ ፕራይድ( KIA SPORTAGE, PRIDE)22
  1. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎች

    ሀ). ሸገር፣ ገላን ከተማ ክፍለ ከተማ፣ ልዩ ስሙ ሲዳ አዋሽ፣ ከኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት ነዳጅ ማደያ አጠገብ በሚገኘው ቤዛ ኢንዱስትሪ ቅጥር ግቢ ዉስጥ ከሰኞ-ቅዳሜ ዘወትር በስራ ሰዓት በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
    ለ). ቀላል ተሽከርካሪዎቹን ፡ አዲስ አበባ፣ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 10 ቤት ቁጥር 198፣ ጴጥሮስ ወ ጳውሎስ ቤተክርስቲያን ጀርባ፣ የድሮው ታይዋን ገበያ መንገድ ባለበት መስመር በሚገኘው ቤዛ ኢንዱስትሪ ቅጥር ግቢ ዉስጥ በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡

  2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራዳ ጊዮርጊስ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር፣ 1000004330793 ገቢ በማድረግ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመክፈል፣ አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፣ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 5058፣ ቦሌ ሚኒ አጠገብ በሚገኘው ሴቪታ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የሐግቤስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ንብረት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ደረሰኙን በማቅረብ ለጨረታዉ የተዘጋጀዉን ሰነድ ከመስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች አንድ እና ከዛ በላይ ተሽከርካሪ ተወዳድረዉ መግዛት ይችላሉ፡፡ ሊገዙ የሚችሉበትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ በቀረበዉ የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ፣ ዕቃ በተናጠል በመሙላት ከ10% (አስር በመቶ)የጨረታና ውል ማስከበሪያ C.P.O. ጋር አያይዘዉ በሰም በታሸገ ፖስታ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ/ም. ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 5058፣ ቦሌ ሚኒ አጠገብ ከሚገኘው ሴቪታ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  4. ጨረታዉ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ/ም፣ ጠዋት 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች/ ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ/ በተገኙበት በሴቪታ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል፡፡ ጨረታዉ ከመካሄዱ በፊትም ሆነ ከተካሄደ በኋላ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብት አለዉ፡፡
  5. ጨረታዉ ከመካሄዱ በፊትም ሆነ ከተካሄደ በኋላ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብት አለዉ፡፡
  6. ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡ 0116 639191 EXT.257/260 ደዉለዉ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ሐግቤስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
አዲስ አበባ

✨ messages.ai_summary
Hagbes invites bids for used vehicles (low bed trailers, cargo trucks, water tank trucks, pickups, light vehicles) and metal water tanks (3000L and 2000L), sold as-is in Addis Ababa. Bidders may buy one or more items. Inspection locations and document purchase details are specified.
Save Tender