አልትሜት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከዚህ በታች የተገለፁትን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች አዲስ አበባ ከተማ ላይ ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
አልትሜት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር: አልት/ ተሽጨ/ 01 /2019
አልትሜት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከዚህ በታች የተገለፁትን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች አዲስ አበባ ከተማ ላይ ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
| ተ.ቁ | ለጨረታ የቀረቡት ተሽከርካሪዎች ዓይነት | ብዛት | |
| 1 | ተሳቢዎች ( Hi-bed and truck trailers) | 03 | በድርጅቱ ስም የተመዘገበ |
| 2 | ዶዉ የጭነት ተሽከርካሪ (DAEWOO CARGO TRUCK) | 02 | በድርጅቱ ስም የተመዘገበ |
| 3 | ዶዉ ተሳቢ ጎታች (DAEWO POWER TRUCK) | 01 | በድርጅቱ ስም የተመዘገበ |
| 4 | ሞሶ ዶዉ ( MUSSO DAEWOO 4 seater) | 01 | በድርጅቱ ስም የተመዘገበ |
| 5 | ማህንድራ ቦሌሮ ፒክ አፕ(MAHINDRA pickup) | 05 | በድርጅቱ ስም የተመዘገበ |
| 6 | ዲስከቨሪ ላንድሮቨር (DISCOVERY) | 03 | በድርጅቱ ስም የተመዘገበ |
| 7 | ላንድሮቨር(LANDROVER) | 07 | በድርጅቱ ስም የተመዘገበ |
| 8 | ዶዉ ቲኮ (DAEWOO TICO) | 04 | በድርጅቱ ስም የተመዘገበ |
| 9 | ዳፍ ተርቦ ከተሳቢው (DAF TURBO with trailor) | 01 | በድርጅቱ ስም የተመዘገበ |
| 10 | ሬንጅ ሮቨር (RANGE ROVER) | 02 | በድርጅቱ ስም የተመዘገበ |
| 11 | ቶዮታ | በድርጅቱ ስም የተመዘገበ | |
| 12 | ቢ.ኤም.ደብሊዉ(BMW) | 01 | በድርጅቱ ስም የተመዘገበ |
| 13 | ዶዉ ኖቨስ የጭነት ተሽከርካሪ (DAEWOO K8CCF NOVUS CARGO TRUCK | 02 | በግለሰብ ስም የተመዘገበ |
| 14 | ተሳቢዎች (truck trailers) | 02 | በግለሰብ ስም የተመዘገበ |
| 15 | ዶዉ ተሳቢ ጎታች (DAEWO V3T8F POWER TRUCK) | 01 | በግለሰብ ስም የተመዘገበ |
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎች በሚከተሉት ሁለት ቦታዎች ከሰኞ -ቅዳሜ ዘወትር በስራ ሰዓት በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
- ሸገር ፣ ገላን ከተማ ክፍለ ከተማ ፣ ልዩ ስሙ ሲዳ አዋሽ፣ ከአዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት ነዳጅ ማደያ አጠገብ በሚገኘው ቢዛ ኢንዱስትሪ ቅጥር ግቢ ዉስጥ
- አዲስ አበባ፣ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 08፣ ስብስቴ ነጋሲ አንደኛ ደረጃ ት.ቤት አጠገብ ወይም ንፋስ ስልክ ፖሊ. ቴክኒክ ኮሌጅ ፊት ለፊት ከሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ ዉስጥ
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል፣ አድራሻ: አዲስ አበባ፣ ንፋስ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 08 የቤት ቁጥር ቤት ቁጥር 297/8 ስብስቴ ነጋሲ አንደኛ ደረጃ ት.ቤት አጠገብ ወይም ንፋስ ስልክ ፖሊ. ቴክኒክ ኮሌጅ ፊት ለፊት ከሚገኘው አልትሜት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ፋይናንስ ክፍል ለጨረታዉ የተዘጋጀዉን ሰነድ ከመስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች አንድ እና ከዛ በላይ ተሽከርካሪ ተወዳድረዉ መግዛት ይችላሉ፡፡ ሊገዙ የሚችሉበትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ በቀረበዉ የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ በተናጠል በመሙላት ከ10% (አስር በመቶ)የጨረታና ዉል ማስከበሪያ C.P.O. ጋር አያይዘዉ በሰም በታሸገ ፖስታ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ/ም. ከቀኑ 6:00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ፣ ንፋስ ክፍለ ከተማ ፣ወረዳ 08 የቤት ቁጥር ቤት ቁጥር 297/8፣ ስብስቴ ነጋሲ አንደኛ ደረጃ ት.ቤት አጠገብ ወይም ንፋስ ስልክ ፖሊ. ቴክኒክ ኮሌጅ ፊት ለፊት ከሚገኘው አልትሜት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ፋይናንስ ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታዉ ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ/ም፣ ጠዋት 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች/ ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በአልትሜት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ጨረታዉ ከመካሄዱ በፊትም ሆነ ከተካሄደ በኋላ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብት አለዉ፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር: 0114 423077 ደዉለዉ ማግኘት ይችላሉ፡፡
አልትሜት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
አዲስ አበባ
✨ messages.ai_summary
Altmet PLC is selling used vehicles by open bid, including cargo trucks, trailers, power trucks, pickups, SUVs, and cars, sold as-is in Addis Ababa. Bidders may inspect vehicles at two sites and may bid for one or more vehicles.
