Tender Detail

Tender Details


ኦርቢስ የንግድ እና ቴክኒክ ማዕከል አ.ማ በመጋዘኑ የቆዩ የተለያዩ አይነት የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን (የመርሴዲስ፣ የቦሽ፣ የሬኖልት፣ የማን) እና የኮሚኒዩኬሽን መሳሪያዎችና መለዋወጫዎች (የሞቶሮላ) እንዲሁም መርሴዲስ ቤንዝ ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Orbis


ያገለገለ ተሽከርካሪ እና መለዋወጫዎች በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

አንጋፋ የአውቶሞቲቭ ኩባንያ ኦርቢስ የንግድ እና ቴክኒክ ማዕከል አ.ማ በኢትዮጵያ ስመጥር የሆኑትን የመርሴዲስ ቤንዝ እና ሬኖልት ተሽከርካሪዎች ብቸኛ አስመጪ መሆኑ ይታወቃል::

በመሆኑም ኩባንያችን በመጋዘናችን የቆዩ የተለያዩ አይነት የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን (የመርሴዲስ፣ የቦሽ፣ የሬኖልት፣ የማን) እና የኮሚኒዩኬሽን መሳሪያዎችና መለዋወጫዎች (የሞቶሮላ) እንዲሁም መርሴዲስ ቤንዝ፣ ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ስለሚፈልግ ህጋዊ ተጫራች የሆናችሁ ሜክሲኮ በሚገኘው መ/ቤታችን ዘወትር በሥራ ሰዓት በመገኘት የመኪኖቹን እና የመለዋወጫዎቹን ዓይነት እና ዝርዝር ማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::

  1. ተጫራቾች ንብረቶቹን ከጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ.ም ከ ጠዋቱ 02:00-10:30 ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ዝቅ ብሎ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በአካል ተገኝተው መመልከት ይችላሉ::
  2. ጨረታው አርብ ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ተዘግቶ በማግስቱ ጥቅምት 6 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋት 04:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
  3. ለጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይቻላል::
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን ዝርዝር መረጃውን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል::
  5. በጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ
  6. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  7. ለበለጠ መረጃ መለዋወጫዎችን በተመለከተ፡ በስልክ ቁጥር፡ 09 13773127 እንዲሁም ተሽከርካሪዎችን በተመለከተ በስልክ ቁጥር 0974656420 ደውለው መረዳት ይችላሉ::

ኦርቢስ ንግድና ቴክኒክ ማዕከል አ.ማ
ስልክ፡ 115516211/ 115510078

✨ messages.ai_summary
Orbis is selling used vehicle spare parts (Mercedes, Bosch, Renault, MAN) and Motorola communication equipment, plus a Mercedes-Benz vehicle, via re-announced tender. Legal bidders may inspect items at the Mexico office during work hours. Tender documents are available for a non-refundable fee.
Save Tender