የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ እቃዎች ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Addis Ababa Abattoirs Enterprise (የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 5/2019
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ እቃዎች ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤
- የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣
- የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣
- የተለያዩ ጀኔሬተሮች ጥገና፣ የላውንደሪ ማሽን፣ የበረዶ ቤት እና የሶፍትዌር የጥገና አገልግሎት፣
ማንኛውም ተጫራች:-
- በዘርፉ ወይም በተመሳሳይ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ከፍያ መለያ ቁጥር(TIN) የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ክሊራንስ እንዲሁም በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር ብር 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በስራ ሰዓት ከግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሠነድ ማግኘት ይችላል፤
- የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድቦንድ/ ለሚጫረትበት የጠቅላላ ዋጋውን 2% በሲ.ፒ.ኦ፣ በባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ በድርጅቱ ደረሰኝ ማስያዝ ይኖርበታል፤
- የጨረታ ሰነዶችና ከጨረታው ጋር ተያያዥ የሆኑ ሠነዶችን በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያው ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፤
- ጨረታው ጥቅምት 19 ቀን 2019ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ውስጥ ይከፈታል:: በጨረታ አከፋፈት ሂደት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉለውም::
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011466-47-05 መጠየቅ ይቻላል::
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
✨ messages.ai_summary
Addis Ababa Abattoirs Enterprise seeks suppliers for vehicle spare parts, electrical materials, generator, laundry machine, cold room and software maintenance services via open tender. Bidders must hold a valid business license, VAT registration, TIN, tax clearance, and supplier registration.
