Tender Detail

Tender Details

  • Company ሬይንቦ የመኪና ኪራይና የአስጎብኚ አገልግሎት ኃ.የተ የግ.ማ
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline28 Oct 2026, 1:00 PM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityየሚፈልጉትን መኪና መነሻ ዋጋ 10% (CPO)
  • opening dateጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በ7:00 ሰዓት
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

ሬይንቦ ኢክስክሉሲቭ የመኪና ኪራይና አስጎብኚ አገልግሎት ኃ.የተ.የግ.ማኅበር ከዚህ በፊት ይጠቀምባቸው የነበሩ አሥራ ሰባት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ሬይንቦ የመኪና ኪራይና የአስጎብኚ አገልግሎት ኃ.የተ የግ.ማ


ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001

ሬይንቦ ኢክስክሉሲቭ የመኪና ኪራይና አስጎብኚ አገልግሎት ኃ.የተ.የግ.ማኅበር ከዚህ በፊት ይጠቀምባቸው የነበሩ አሥራ ሰባት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ የጨረታው መመሪያዎች፡-

  1. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከድርጅቱ በመግዛት በባንክ አካውንት ቁጥር በዳሽን ባንክ 0122001545005 ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000317295484 የማይመለስ ብር 500.- (አምስት መቶ ብር) ገቢ አድርገው ደረሰኙን በማቅረብ ሣር ቤት አዳምስ ፋቢሉን ወደ ቁራ በሚወስደው መንገድ ኪያብ ህንፃ 5ኛ ፎቅ መውሰድ ይኖርባቸዋል::
  2. ተሽከርካሪዎቹን ለሚት ፋርማኪዩር ግቢ ውስጥ በአካል ቀርበው መመልከት ይችላሉ::
  3. ተጫራቾች የሚፈልጉትን የመኪና አይነትና የሠሌዳ ቁጥር ከሚገዙበት ዋጋ ጋር በመጥቀስ እና ለጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የሚፈልጉትን መኪና መነሻ ዋጋ 10% (አሥር በመቶ) በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በማያያዝ ከሰኞ እስከ አርብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 5:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  4. ተጫራቾች ሊገዙ የሚፈልጉትን ተሽከርካሪ የሚያቀርቡትን ዋጋ በተዘጋጀው የሚገዛበት ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በግልጽና በማያሻማ ሁኔታ በመሙላት በስም በታሸገ ፖስታ ከተው ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ማግስት ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በዋናው መ/ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) ያካተተ መሆን ይኖርበታል::
  6. አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው ነገር ግን አንድ ተጫራች ለእያንዳንዱ መኪና የጨረታ ማስከበሪያ የተጠየቀውን ሲፒኦ በማቅረብ ከአንድ መኪና በላይ መጫረት ይችላል::
  7. ጨረታው ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በ7:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለሚት ፋርማኪዩር ግቢ ውስጥ ይከፈታል::
  8. በጨረታው ለሚሸነፉ ተወዳዳሪዎች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ይመለስላቸዋል:: ለአሸናፊዎች ግን ከግዢው ክፍያ ላይ ታሳቢ ይሆናል::
  9. ድርጅቱ መኪኖቹን ለመሸጥ የሚያስፈልጉ ክሊራንስ በራሱ ወጪ ከሚመለከተው መንግስት መ/ቤት ያቀርባል::
  10. የጨረታ አሸናፊዎች የስም ማዛወሪያና በሽያጩ ምክንያት የሚጣለውን ማናቸውንም ግብር፣ ቀረጥና የተሽከርካሪው የሽያጭ ግምት ክፍያ እንዲሁም ለሚገዟቸው መኪናዎች ማናቸውንም ተዛማጅ አገልግሎቶች ወጪ ሙሉ በሙሉ በራሳቸው ይሸፍናሉ::
  11. የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበትን የመኪና ዋጋ ከፍለው በሰባት (7) የሥራ ቀናት ውስጥ መኪኖቹን ማንሳት አለባቸው:: ይህ ሳይሆን ቢቀር ያስያዙት ገንዘብ /ሲ.ፒ.ኦ/ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ከጨረታው አሸናፊነት ይሰረዛሉ::
  12. የጨረታ አሸናፊዎች በሦስት ወራት ውስጥ የባለቤትነት ስም ዝውውር መጨረስ አለባቸው::
  13. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ

አድራሻችን:- ሣር ቤት አዳምስ ፋቢሉን ዝቅ ብሎ ወደ ቁራ በሚወስደው መንገድ በኪያብ ህንፃ 5ኛ ፎቅ ወይም

በስልክ ቁጥር 011 372 26 38 ወይም 011 371 79 44 ወይም 011 372 26 40

ኢ-ሜይል Info@rainbowethiopiatours.com አዲስ አበባ

ሬይንቦ የመኪና ኪራይና የአስጎብኚ አገልግሎት ኃ.የተ የግ.ማ

✨ messages.ai_summary
Rainbow car rental and tour service invites bids to sell 17 used vehicles as-is. Bidders buy the tender document, inspect vehicles at Lmit Pharmacure compound, and submit bids with a 10% CPO per vehicle. Prices must include 15% VAT. Winners cover transfer taxes and must collect vehicles within 7 working days.
Save Tender