በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የለሚ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የተለያዩ የአካፋይ መንገድ አጥር፣በከተማ ውስጥ ለሚሰራው ጠጠር መንገድ የኮንስትራክሽን ማሽን ኪራይ እና ዳምፕ ትራክ ገልባጭ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የለሚ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የለሚ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የተለያዩ የአካፋይ መንገድ አጥር፣በከተማ ውስጥ ለሚሰራው ጠጠር መንገድ የኮንስትራክሽን ማሽን ኪራይ እና ዳምፕ ትራክ ገልባጭ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡በመሆኑም ተጫራቾች ለመወዳደር የሚያሟሏቸው መስፈርቶች
- በየዘርፉ የታደሰ የንግስ ስራ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያቁጥር /TIN/ ያላቸው
- የማንባታ ዘርፉ ከብር 200000 ሺህ በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው
- ተጫራቾች የደረጃ 7 እና በላይ የኮንስትራክሽን ላይሰንስ የብቃት ማረጋገጫ እና የማሽን ኪራይ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ከውሀ ተቋራጭ ስራ ዘርፍ ውጭ መሆን አለባቸው
- ተጫራቾች ለኮንስትራክሽን ማሽን ኪራይ BC/rode construction/ ፋቃድ ያላቸው
- ለዳምፕ ትራክ/ገልባጭ ተጫራቾች የደረቅ ጭነት ንግድ ፍቃድ መሆን አለበት
- ለኮንስትራክሽን ማሽን ኪራይ እና አካፋይ መንገድ አጥር ግንባታ GC/ general consturaction. ፋቃድ ያላቸው
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የእቃ ወይንም አገልግሎት ጠቅላላ ብር 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ትእዛዝ CPO ወይም ጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ህጋዊ ደረሰኝ /መሒ1 ተቆርጦ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማስያዝ ይኖርባቸዋል
- የጨረታው ሰነዱን በአግባቡ ኮፒና ኦርጅናሉን በመለየት በየገፁ ተፈርሞበት ማህተም ተቀምጦበት በተለያየ ፖስታ በማሸግ ኮፒውን ኮፒ ኦርጅናሉን ኦርጅናል በማለት መለየት ያስፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት የጨረታ ሰነድ ላይ ማንኛውም ስርዝ ድልዝ ካለው ወይንም ለሶስተኛ ወገን ግልጽ ካልሆነ ሰነዱ ውድቅ ይሆናል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የንግድ ፍቃድ የTIN ምዝገባ ተወካይ ከሆኑ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ሌሎችም ማስረጃዎች ከኦርጅናል ሰነድ ጋር በፖስታ ውስጥ መግባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ብሔራዊ በዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከቢሮ ቁጥር 5 ላይ የማይመለስ 500 ብር እየከፈሉ መግዛት ይችላሉ
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በመ/ቤታችን ግዢ ቢሮ ቁ5 በ16ኛው ቀን 4፡00ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- የታደሰ የማሽን ኪራይ እና የኮንስትራክሽን ኪራይ ላይሰንስ ያለው መሆን አለበት፡፡
- ጨረታውን ለማባዛት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነው፡፡
- የአከፋይ መንገድ አጥር ግንበታ ጨረታውን የምናጫርተው በሎት ሲሆን የኮንስትራክሽን ማሽን ኪራይ በነጠላ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
የለሚ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት
✨ messages.ai_summary
Lemi Town Municipality seeks bidders for akafay road fencing, construction machine rental for gravel road works, and dump truck tipping. Bidders need renewed licenses, TIN, VAT registration, Grade 7+ construction license, and machinery rental permits.
