አንድነት ቅቤና ቅመማ ቅመም አክሲዮን ማኅበር ለ2019፣ 2020 እና 2021 በጀት ዓመት የሚሠራባቸውን የድርጅቱ ሂሳብ ኦዲት የሚያደርግ ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
አንድነት ቅቤና ቅመማ ቅመም ነጋዴዎች አክሲዮን ማኅበር
ለኦዲት ሥራ የወጣ ማስታወቂያ
አንድነት ቅቤና ቅመማ ቅመም አክሲዮን ማኅበር ለ2019፣ 2020 እና 2021 በጀት ዓመት የሚሠራባቸውን የድርጅቱ ሂሳብ ኦዲት የሚያደርግ ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተወዳዳሪ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላል፡፡
- በኦዲት ሥራ ንግድ ፈቃድ ያለው፣
- የዘመኑ ግብር የከፈለ፣
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፣
- የተ.እ. ታክስ (ቫት) ሰርተፍኬት፣
- ከዚህ በፊት ቢያንስ የአምስት ድርጅቶች ሂሳብ ኦዲት ስለማድረጉ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 5000.00 ( አምስት ሺ ) ብር በአክሲዮን ማኅበሩ ስም ሲ.ፒ.ኦ. (CPO) አሠርቶ ማቅረብ አለበት፣
- የጨረታውን ዶክሜንት የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ ) ብር ከፍሎ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው የሥራ ቀን 2ኛ ፎቅ ከሚገኘው ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ፣
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ የሚሠሩበትን ዋጋ በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዕለቱ 6:00 ተዘግቶ ከቀኑ በ8:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአክሲዮን ማኅበሩ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
- አክሲዮን ማኅበሩ ለጨረታው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ቅቤና ቅመማ ቅመም አክሲዮን ማኅበር
መርካቶ ቃኛው ሻለቃ ሆቴል ጀርባ
ስልክ ቁጥር፡- 09 11 68 49 04 ወይም 09 83 02 73 79
አንድነት ቅቤና ቅመማ ቅመም ነጋዴዎች አክሲዮን ማኅበር
✨ messages.ai_summary
Andinet Butter and Spice Traders Share Company seeks a licensed audit firm to audit its accounts for three fiscal years. Bidders must have an audit business license, tax compliance, commercial registration, VAT certificate, and proof of auditing at least five organizations.
