ኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው ኤሌክትሮኒክስ፣ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ አዳዲስ አልባሳት፣ ኮስሞቲክስ፣ ሽቀጣሽቀጥ (ልዩ) እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ግ-06/2019 ዓ.ም
ኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው ኤሌክትሮኒክስ፣ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ አዳዲስ አልባሳት፣ ኮስሞቲክስ፣ ሽቀጣሽቀጥ (ልዩ) እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-
- ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በአክሽን ኢትዮጵያ አንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም፡፡
- በግልፅ ጨረታ ላይ የወጡትን ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ሳያስፈልገው በብሔራዊ መታወቂያ ብቻ የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopla) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች አክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በሥራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2:00-6:00 ሰዓት መመልከት ይቻላል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚወጣበት ቀን እና ጨረታው የሚያበቃበት ቀን እና ሰዓት የሚያሳይ ሰንጠረዥ፡-
| ተ.ቁ | የእቃው አይነት | የጨረታው አይነት | በአዲስ ዘመን የታተመበት ቀን | ጨረታው የሚካሄድበት ቀን | ጨረታው የሚዘጋበት ቤት ሰዓት | ጨረታው የሚከፈት ቤት ሰዓት |
| 1 | አዳዲስ አልባሳት | ግልፅ | 30/01/2019 | 07/02/2019 | 4:00 | 4:30 |
| 2 | ኤሌክትሮኒክስ | ግልፅ | 30/01/2019 | 07/02/2019 | 4:00 | 4:30 |
| 3 | ኮስሞቲክስ | ግልፅ | 30/01/2019 | 07/02/2019 | 4:00 | 4:30 |
| 4 | ተሽከርካሪ መለዋወጫ | ግልፅ | 30/01/2019 | 07/02/2019 | 4:00 | 4:30 |
| 5 | ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች | ግልፅ | 30/01/2019 | 07/02/2019 | 4:00 | 4:30 |
| 6 | ሽቀጣ ሽቀጥ(ልዩ ልዩ) | ግልፅ | 30/01/2019 | 07/02/2019 | 4:00 | 4:30 |
ስልክ ቁጥር: 0221118429/ 0222118925
- በግልፅ ጨረታ ሽያጭ ላይ የእቃዎቹ እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች አስመጪ ወይም የአስመጪ ቤተሰብ መሳተፍ አይችሉም፡፡ ነገር ግን በጨረታው ተሳትፈው ቢገኙ በሕግ ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡
- በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ምድብ እቃዎች እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለት (CPO) (Customs commission Adama Branch) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሠራት ያሠሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ አክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የወጡት እቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የመንግሥት ጉምሩክ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 እንዲሁም ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች መሥሪያ ቤቱ አዳማ ቆርቆሮ አካባቢ በተከራየው መጋዘን ቁጥር 5 ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ለግልፅ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በስምንተኛው ቀን 4:00 ሰዓት ጨረታው ይዘጋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን ፣ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 /ሶስት/ የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ በተ/ቁ 10 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
- ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም፡፡
- ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሠሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን፡፡
የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09- 05-11-5511/ 011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- አዳማ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን የስራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች 0221118429 እና 0222118925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Ethiopia Customs Commission Adama branch invites bids to buy seized electronics, vehicle spare parts, new clothes, cosmetics, assorted goods, and used motorcycles. Bidding is via the Auction Ethiopia app or auction.et. Bidders need a renewed trade license, VAT registration, and tax clearance; for used motorcycles, any Ethiopian over 18 with a national ID may bid.
