Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ወሎ ዞን የጃማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ደቡብ ወሎ ዞን የጃማ ወረዳ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 033-226-01-64
  • Website
  • Deadline20 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300(ሶስት መቶ ብር)
  • Bid Securityበሎት: ከብር 2,500 እስከ 35,500 (CPO/የባንክ ዋስትና/በጥሬ ገንዘብ)
  • opening dateበዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 8:30 ይከፈታል
  • Categories Veterinary Equipment And Supplies , Computer Laptop And Accessories , Stationery Materials

በደቡብ ወሎ ዞን የጃማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን የጃማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ወሎ ዞን የጃማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 -ወረቀትና የወረቀት ውጤቶች፣ ሎት 2 የፅሕፈት መሳሪያ ፣ ሎት 3 የኮምፒውተር መሳሪያዎች ፣ ሎት 4- የኤሌክትሪክ መሳሪያዎች ፤ ሎት 5 ፈርኒቸር ፣ ሎት 6- የፅዳት እቃ ፣ ሎት 7 የውሃ እቃ ፣ ሎት 8 የሞተር እቃዎች፣ ሎት 9 የመኪና መለዋወጫ ፋስት ሙቪንግ እቃ ፣ ሎት 10 የመኪና ጎማ በተጨማሪም በሪቮልቪንግ ፈንድ በጀት ሎት 11 እንስሳት መድሃኒት ፤ ሎት 12 የእንስሳት ህክምና መገልገያ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ ።

  1. ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ።
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችል ።
  4. የግዥ መጠን ብር ከ500,000 (አምስት መቶ ሺ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡
  6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስማቸውን፤ ፊርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር እና የድርጅቱ ማህተም ማሳረፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ከጨረታ ውድቅ የሚያደርግ መሆኑን አዉቀዉ በጥንቃቄ መሙላት ይጠበቅባቸዋል ።
  8. ተጫራቾች የሚቀርቡትን የእቃው አይነት ዝርዝር መግለጫ ወይም እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ በተጨማሪም መ/ቤቱ ባስቀመጠው ናሙና መሰረት መሞላት አለበት፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ ሎት 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በመ/ቤታችን ረዳት ገ/ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 13 እና 14 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ ለሎት1-ወረቀትና የወረቀት ውጤቶች 22,500(ሃያ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) ፤ ለሎት 2 የፅህፈት መሳሪያ 23,100/ሃያ ሶስት ሺህ አንድ መቶ ብር) ለሎት 3 የኮምፒውተር መሳሪያዎች 35,500 (ሰላሳ አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር) ፤ ለሎት 4 ኤሌክትሪክ እቃዎች 2,500/ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር፣ ለሎት 5 ፈርኒቸር 14,500 አስራ አራት ሺህ አምስት መቶ ብር ፤ ለሎት 6 የፅዳት እቃ 7,500 (ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር) ፤ ለሎት7 የውሃ እቃ 35,500/ሰላሳ አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር ፤ ለሎት 8 የሞተር እቃዎች 4,500 አራት ሺህ አምስት መቶ ብር ፤ ለሎት 9 የመኪና መለዋወጫ ፋስት ሙቪንግ እቃ ለእያንዳንዳቸው መኪና / ተሽከርካሪ/ ሞዴል 7,500 ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር ፤ ለሎት 10 የመኪና ጎማ 3,500 ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር፣ ለሎት 11 እንስሳት መድሃኒት 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ፤ ለሎት 12 የእንስሳት ህክምና መገልገያ እቃዎች 6,500 ስድስት ሺህ አምስት መቶ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ በመ/ሂ 1 ማስያዝ አለባቸው፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ኦርጅናልና ፖስታ ጥንቃቄ በማሸግ በጃማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል
  12. ከጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን በ 8:00 ይዘጋል ። በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 8:30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበአል ቀን እና ካሎት አምስት የስራ ቀናት ዉጭ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል ።
  13. መ/ቤቱ በጨረታው በሚገዙ ግዥው ላይ 20% የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
  14. ከማንኛውም ተጫራች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም ።
  15. ማንኛውም ተጫራቾች ግዥው በጥቅል / በሎት/ የሚፈፀም መሆኑን አውቆ ለእያንዳንዱ ዝርዝር እቃወች ዋጋ መሙላት ይኖርበታል፡፡ ሎት 9 የመኪና መለዋወጫ ፋስት ሙቪንግን በተመለከተ አሸናፊ የሚለየው በእያንዳንዱ መኪና ሞዴል ሲሆን የተዘረዘሩት እቃወች በሙሉ ጠቅላላ ለእያንዳንዳቸው ዋጋ ያለመሙላት ከጨረታው ውድቅ ያደርጋል ። እንዲሁም አሸናፊ የሆነ ተጫራች ያሸነፋባቸዉን እቃዎች ሙሉ በሙሉ ሳያጠናቅቁ ክፍያ የማይፈጸም መሆኑን እና በውለታው መሰረት እቃውን ጨርሰው ለመ/ቤቱ የማስረከብ ግዴታ አለባቸው ።
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  17. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም
    በስልክ ቁጥር 033-226-01-64 ወይም 033-226-01-44 በመደወል ማግኘት ይችላል፡

በደቡብ ወሎ ዞን የጃማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Jamma District Finance Office invites bids for supplies for local offices: paper, stationery, computers, electrical items, furniture, cleaning and water supplies, motor and vehicle spare parts, tires, veterinary drugs and equipment. Bidders need valid license, tax and VAT proof, TIN, and sealed documents.
Save Tender