በደቡብ ኢት/ያ ክልል የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት በጨረታ ቁጥር ሶከፋ/01/2019 ዓ/ም ፍራሽ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢት/ያ ክልል የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት በጨረታ ቁጥር ሶከፋ/01/2019 ዓ/ም ፍራሽ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- የጨረታ ቁጥር ሶከፋ/01/2019 ዓ/ም ፍራሽ ግዥ ጨረታዉን ለመሳተፍ የሚፈልጉት፡-
- በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉት በሚመለከታቸዉ መስሪያ ቤቶች በአቅራቢነት የተመዘገቡና ለ2019 በጀት ዓመት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና በ EGP የተመዘገቡ፣ ከዚህ በፊት ላከናወናቸዉ ተመሳሳይ ሥራዎች /አገልግሎቶች ከአሠሪዉ አካል የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት (አስራ አምስት ቀናት) ከታች ከተጠቀሰዉ አድራሻ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የተዘጋጀዉን መደበኛ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በማቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር ዋና ሥራ ሂደት ቢሮ ይገኛል፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛዉ ቀን ከቀኑ 4:00 (አራት ሰዓት) ድረስ ለጨረታዉ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረዉም ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለስለታል፡፡
- ጨረታዉ የሚከፈተዉ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉና ሌሎች መገኘት የሚፈልጉ ባሉበት በ16ኛዉ ቀን ከቀኑ 4:00 ላይ ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 4:30 የሚከፈት ይሆናል፡፡ 16ኛዉ ቀን የበአላት ቀን ከሆነ (የሥራ ቀን ካልሆነ) በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ርክክብ የሚፈጸምበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ቅጥር ግቢ ዉስጥ ይሆናል፡፡
- የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ: 0461800863 ደዉሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ
✨ messages.ai_summary
Wolaita Sodo City Administration Finance and Plan Development Department seeks to buy mattresses through open tender. Bidders must be registered suppliers with a renewed trade license, VAT registration, supplier certificate, EGP registration, and proof of good performance on similar past work.
