በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በወረዳ 04 ት/ጽ/ቤት የዱዱቢሳ የመ/ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለሥራ የሚያስፈልጉ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሠራት ይፈልጋል።
በአዲስ አባበ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የዱዱቢሳ 1ኛ ድረጃ ት/ቤት
የግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በወረዳ 04 ት/ጽ/ቤት የዱዱቢሳ የመ/ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለሥራ የሚያስፈልጉ እቃዎች ማለትም ሎት1 የትምህርት እቃዎች፣ ሎት2 የቢሮ እቃዎች፣ ሎት3 የፅዳት እቃዎች፣ ሎት4 የደንብ ልብስ፣ ሎት 5 ፈርኒቸሮች፣ ሎት6 ፕላንት ማሽነሪ ሎት 7 ልዩልዩ መሣሪያዎች፣ ሎት 8 የኤሌክትሮኒክስ ማሽነሪ ጥገና፣ ሎት 9.የትራንስፖርት እቃ ጭነት ሥራ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሠራት ይፈልጋል።
በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ለተጠቀሱት እቃዎች በዘርፉ የደንብ ሥራ ላይ የተሰማሩ መሆን አለባቸው።
1.1.በዘመኑ በ2019 የታደሰ ንግድ ፍቃድና በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፣የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ከሆኑ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN NO / ያላቸው።
ተጫራቶች በአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ድረገጽ በአቅራቢዎች በተዘጋጀው ክፍል የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
2.1. ማንኛውም ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩትን ሰነዶች ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በመለየት ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ በፖስታ በማሸግ ማስገባት አለበት ። ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ የኢትዮጵያ ብር የክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ከኦርጅናል ጨረታ ሰነድ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት፡
- ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ከት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 1 የማይመለስ 400.00 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመግዛት የሚጫረቱበት ዋጋ በሰነድ ላይ በግልፅ በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ኮፒና ኦርጂናል ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 9 መጫረት ወይም መርጠው አንዱን ወይም ሁሉቱን መጫረት ይችላሉ ነገር ግን ከእያንዳንዱ ሎት እቃዎች መራርጠው ለተወሰኑት እቃዎች ብቻ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም ።
- የጨረታው ሳጥን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ሆኖ በአስረኛው ቀን በ3:30 (ሶስት ሰዓት ተኩል ) ታሽጎ በ4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።
- ት/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል ለመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
- ዱዱቢሳ የመ/ደ/ት/ቤት በግልፅ ጨረታ የተለያዩ የፅዳት ዕቃ፣ የትምህርት እቃዎች፣ የቢሮ እቃዎች፣ ደንብ ልብስ፣ ፕላንት ማሽነሪ፣ ፈርኒቸሮችና ልዩ ልዩ መሣሪያዎች፣የ ኤሌክትሮኒክስ ማሽነሪ ጥገና ፤9.የትራንስፖርት እቃ ጭነት በሠንጠረዥ በቀረበው መሰረት የምትጫረቱበትን ዋጋ ሻጉን በመጨመር ሞልታችሁ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
1.የተጫራቾች መመሪያ
1.2.ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት፣ የአቅራቢነት የምዝገባ ሠርተፊኬት ቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ ሰርተፊኬት የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
1.3. ተጫራቾች ከአንድ መቶ ሺህ (100,000.00) ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ዕቃዎች የሚጫረቱ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
1.4.በተ.ቁ 1.2 የተዘረዘሩትን ሠነዶች እያንዳንዳቸው ላይ በአንድ ገጽ ላይ በግልፅ በሚነበብ ሁኔታ ኮፒ በማድረግ በኦሪጅናሉ በማመሳከር ማስገባት አለባቸው፡
1.5. የጨረታ ሰነድ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ከሎት 1 እስከ 9 የተዘረዘሩት ዕቃዎች በተዘረዘረው ሠንጠረዥ መሰረት የሚጫረቱበትን ዋጋ በትክክል በመሙላት መሪያም በሚገባቸው ቦታ ላይ በመፈረም በማሕተም ቦታ ማሕተማቸውን በማድረግ በስም በታሸገ ፖስታ ማስገባት አለባቸው።
1.6 ት/ቤቱ ያዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ትተው በሌላ በራሳቸው ሰነድ ዋጋ የሚያቀርቡ ተጫራቾችን ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ።
1.7 ተጫራቾች ናሙና ያቀርባሉ ተብለው የተዘረዘሩትን እቃዎች ጨረታ ከመዘጋቱ በፊት በማቅረብ እና በማስመዝገብ ማስረከብ አለባቸው።
1.8 ናሙናዎቹ ለተሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊው እንደተገለጸ ይመለስላቸዋል። ለአሸናፊዎች ተጫራቾች ግን እቃዎችን አስረክበው እስኪያጠናቅቁ ድረስ ለማመሳከሪያነት ቆይተው አስረክበው ተመላሽ ይሆናል።
1.9 የጨረታው ሳጥን በት/ቤቱ የሚገኝ ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ማስገቢያ ቀንና ሰዓት ከመጠናቀቁ በፊት በስራ ቀንና ሰዓት ሰነዶችን ማስገባት አለባቸው።
1.10 የት/ቤቱ የጨረታው ኮሚቴ ዕቃዎቹን የሚመርጠው ዝቅተኛ ዋጋ በማየት ብቻ ሳይሆን ጥራቱን መሰረት ያደረገ መሆኑን በመገንዘብ ናሙና ሲያቀርቡ ጥራቱ የጠበቀ እቃ ማቅረብ አለባቸው።
1.11 በጨረታው ሰነድ ላይ ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዮችን ማብራሪያ የሚፈልጉ በጽሁፍ ወይም በአካል በስራ ቀንና ሰዓት በት/ቤቱ በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ።
1.12 ከተገለጸው ቀንና ሰዓት በኋላ የሚመጡ ተጫራቾች አይስተናገዱም።
1.12.1 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ሲ.ፒ.ኦ) ከዚህ በታች በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው።
| ሎት ቁጥር | የሎት ዝርዝር | የጨረታ ሰነድ ገዢ የማይመለስ ብር | የተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በኢትዮጵያ ብር |
| ሎት-1 | አላቂ የትምህርት ዕቃዎች | 400 | 30000 |
| ሎት-2 | አላቂ የቢሮ ዕቃዎች | 400 | 40000 |
| ሎት-3 | አላቂ የጽዳት ዕቃዎች | 400 | 30000 |
| ሎት-4 | የደንብ ልብስ | 400 | 50000 |
| ሎት-5 | ፈርኒቸሮች | 400 | 60000 |
| ሎት-6 | ፕላንት ማሽነሪ | 400 | 60000 |
| ሎት-7 | ልዩ ልዩ መሳሪያዎች | 400 | 50000 |
| ሎት-8 | የኤሌክትሮኒክስ ማሽነሪ ጥገና | 400 | 30000 |
| ሎት-9 | የትራንስፖርት እቃ ጭነት | 400 | 30000 |
የኢትዮጵያ ብር 10,000 (አስር ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ለት/ቤቱ ማስያዝ አለባቸው። የጨረታው ማስከበሪያ ለአሸናፊ ተጫራቾች ሲፒኦ የሚመለሰው የጨረታ ሂደት ካለቀ በኋላ መሆኑን እናሳውቃለን።
1.13 አሸናፊ ተጫራች ለውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ 10% (አስር ፐርሰንት) የማስያዝ ግዴታ አለበት ።
1.14 ተጫራቾች ላለማጭበርበር እና ሙስና ላለመፈጸም ከጨረታ ሰነድ ጋር የተያያዘውን ቅጽ መፈረም አለባቸው።
1.15 የጨረታ ሂደቱን ለማዛባት መሞከር ከጨረታ ወጪ ከማድረጉ በተጨማሪ ለወደፊት በመንግሥት ግዢ እንዳይሳተፍ ያደርጋል።
1.16 አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መፈረም አለበት። በውል አፈጻጸም ወቅት ከገበያ ዋጋ መቀነሱ ምክንያት ያሸነፈው ድርጅት የዋጋ ቅናሽ ማድረግ ይችላሉ። ግን ዋጋ ጭማሪ ማድረግ አይችሉም።
1.17 አሸናፊው ድርጅት የውል መሰረት ግዴታውን ሳይፈፅም ከቀረ ውል ማስከበሪያ ይወረሳል።
1.18 አሸናፊው ድርጅት ለቅድመ ክፍያው ተመጣጣኝ ዋስትና ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ ቼክ ወይም በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለበት።
1.19.ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ቀን ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2:30 እስከ 6:30 እና ከሰዓት በኋላ 7:30 እስከ 11:30 መሆኑን እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ :- ሲ.ፒ.ኦ የምታሰሩት በዱዱቢሳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ስም መሆኑን እናሳውቃለን።
የት/ቤቱ አድራሻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ልዩ ስሙ ቦሌ አራብሳ ጨርቆስ አደባባይ ለሚ እንጀራ ማዕከል ፊት ለፊት መሆኑን እንገልጻለን።
