ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ (መኪና፣ የውሃ ቱቦ፣ ሞተር ሳይክሎች፣ ቆራሌ ብረቶች እና ሌሎች) - ወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ወረዳው በተለያዩ ጊዜ በግዥ በዕርዳታና በስጦታ ያገኛቸዉ ያገለገሉ ንብረቶችን ማለትም ያገለገለ መኪና፣ የውሃ ቱቦ ባለብረት የተለያዩ እንች ፤ የሞተር ሳይክሎች፤ ቆራሌ ብረቶች እና ሌሎች ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
- የዘመኑ የታደሰ ማንኛውም ዓይነት ህጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000/አንድ መቶ ሽህ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር ጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለዶክመንቱ የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ/ በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ሥራ ሂደት /ክፍል/ በመውሰድ ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ አንድ ኦሪጂናልና አንድ የኦሪጂናል ኮፒ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከገዙ በኋላ ከጨረታው ቀን በፊት ንብረቶቹን በአካል ለማየት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ እንደተረጋገጠ ያሸነፉትን ዋጋ በኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ መደበኛ አካውንት ሙሉ በሙሉ ገቢ ሲያደረግ ያሸነፈውን ንብረት ወዲያውኑ ይረከባል፡፡ ሌሎች ዝርዝር ሂደቶች በጨረታ ሰነዱ የሚካተቱ ይሆናል፡፡
- የመኪና እና ሞተር ተሽከርካሪዎች ስም ዝውውር በገዥ ይሸፈናል፣ የተሽከርካሪዎች ታሪክ ማስረጃ መ/ቤቱ ለገዥው ያቀርባል፡፡ ሌሎች ንብረቶች የይለፈ ደብዳቤ ይሰጣል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናቶች ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ በ 22ኛው ሥራ ቀን ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 5፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም ይከፈታል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09-16-59-96-57/ 09-16-35-11-13/-09-25-14-75-81 ይደውሉ፤
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Sale of used government assets—vehicles, water pipes, motors, motorcycles, scrap metal and other items—by Wolaita Zone Kindo Koysha Woreda Finance Office. Bidders need a valid business license, TIN, and VAT registration.
