ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ (ብሪጅስተን ጎማ 7.50 R16 እና የተለያዩ መለዋወጫዎች) - ካርተር ሴንተር ኢትዮጵያ (The Carter Center)
The Carter Center Ethiopia
ካርተር ሴንተር ኢትዮጵያ
የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ካርተር ሴንተር ኢትዮጵያ (TCC-E) በተለያዩ የጤና ዘርፎች ላይ የሚሰራ ዓለም አቀፍ ድርጅት ሲሆን፣ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በተለያዩ ጊዜያት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ያገለገሉ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
| ቁጥር | የሚሸጠው ንብረት ዓይነት | መስፈሪያ | ብዛት |
| 1 | ብሪጅስተን ጎማ 7.50 R16 114/112N (Jamal) | ቁጥር | 174 |
| 2 | የተለያዩ መለዋወጫዎች | ጥቅል | 257 |
ማሳሰቢያ: በተራ ቁጥር 2 ላይ የተጠቀሰውን የዕቃ አይነት ዝርዝር በድርጅቱ ቅጥር ጊቢ በመገኘት ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
- የሰነድ መግዣ ቦታ፡- ፍላጎቱ ያላቸው ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን በካርተር ሴንተር ኢትዮጵያ ዋና መሥሪያ ቤት (አዲስ አበባ፣ ቦሌ ንዑስ-ከተማ፣ ወረዳ 06፣ ገርጂ መብራት ኃይል፣ ሙልሙል ዳቦ ቤት አጠገብ)፣ የሎጂስቲክስና ግዢ ክፍል ቢሮ ቁጥር 110 በመገኘት ማግኘት ይችላሉ።
- ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ፡- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዳቸውን እስከ ጥቅምት 4 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ ቢሮ ውስጥ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ጊዜ፡- ጨረታው ጥቅምት 4 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 04፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት ይከፈታል።
- የካርተር ሴንተር ኢትዮጵያ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጫረታው የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች በሚከተለው አድራሻ ላይ ተጨማሪ መረጃ ሊያገኙ ይችላሉ፡-
አድራሻ
ካርተር ሴንተር ኢትዮጵያ
ቦሌ ክ-ከተማ፣ወረዳ 06 ቤት ቁጥር: አዲስ
የሎጂስቲክስ እና ግዢ ክፍል
ፖስታ ሳጥን: 13373, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ
ስልክ ቁ. +251-11663-18 63 ወይም +251-11662 45 62
✨ messages.ai_summary
The Carter Center Ethiopia seeks to sell used property by open bid: 174 Bridgestone tires (7.50 R16 114/112N) and 257 bundles of assorted spare parts. Bidders may inspect the spare parts list at the organization's premises. The Carter Center reserves the right to cancel the bid in part or in full.
Not stated in the notice: bid security, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
