Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address በቦሌ ሚካኤል መንገድ በካርጎ ቅጥር ግቢ ውስጥ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116651351
  • Website
  • Deadline12 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceየማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ)
  • Bid Securityግልጽ ጨረታ: የሰጡትን ዋጋ 5% (CPO)፤ ሐራጅ: ብር 100.00 ለየዘርፉ
  • opening dateበዛው ቀን በ8፡15
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

የተወረሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ (ግልጽና ሐራጅ ጨረታ ቁጥር 28/2019 - 36/2019) - በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ልዩ ልዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 28/2019፣ 29/2019፣ 30/2019፣ 31/2019፣ 32/2019፣ 33/2019፣ 34/2019፣ 35/2019 እና 36/2019 ለመሸጥ ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜያት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ባለመፈጸም ምክንያት እና በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሞባይሎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጌጣጌጥ እና አካላት፣ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ ጊርቦክስ እና ሌሎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ እና በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 28/2019 በቀን 2/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 29/2019 በቀን 05/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 30/2019 በቀን 09/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 31/2019 በቀን 12/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 32/2019 በቀን 16/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 33/2019 በቀን 19/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 34/2019 በቀን 23/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 35/2019 በቀን 26/02/2019፣ ጨረታ ቁጥር 36/2019 በቀን 30/02/2019 ዓ.ም በመሆኑ የቀጣይ 2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በተፈለገው መጠን ለማሳካት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

ጨረታ ቁጥርቀን
28/20192/02/2019 ዓ.ም
29/201905/02/2019 ዓ.ም
30/201909/02/2019 ዓ.ም
31/201912/02/2019 ዓ.ም
32/201916/02/2019 ዓ.ም
33/201919/02/2019 ዓ.ም
34/201923/02/2019 ዓ.ም
35/201926/02/2019
36/201930/02/2019 ዓ.ም

በመሆኑም

  1. በቅ/ጽ/ቤቱ ለሚካሄደው ጨረታ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የተከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 - 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 - 11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 - 6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ ጉምሩክ መጋዘን ቅጥር ግቢ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ(5%) ዋስትና (CPO) CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOM BRANCH OFFICE ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ካርጎ መጋዘን እና ገርጂ መጋዘን ጥቅምት 02/2019 ዓ/ም፣ ጥቅምት 05/2019 ዓ.ም፣ ጥቅምት 09/2019 ዓ.ም፣ ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም፣ ጥቅምት 16/2019 ዓ/ም፣ ጥቅምት 19/2019 ዓ/ም፣ ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም፣ ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም፣ ጥቅምት 30/2019 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ተዘግቶ በዛው ቀን በ8፡15 የሚከፈት ይሆናል።
  5. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ለጨረታው የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዘው በቀረቡት ቅጾች መሠረት ለመረጡት የዕቃዎች ኮድ የተሰጠ ዋጋ፣ የተጫራቾች ስም፣ አድራሻ፣ ፊርማና የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ(CPO) እና ከላይ በተ.ቁ 1 የተገለጹትን ሰነዶች ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ ላይ በመፈረም አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ የሰጠውን መግዣ ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም።
  7. ማንኛውም ተጫራች የሰጠውን የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ የጨረታው ውጤት እስከሚታወቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
  8. የጨረታው አሸናፊዎች ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ በ05 (አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለባቸው።
  9. ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰደ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

    በተራ ቁጥር 01 - 09 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 28/2019 በቀን 2/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 29/2019 በቀን 05/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 30/2019 በቀን 09/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 31/2019 በቀን 12/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 32/2019 በቀን 16/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 33/2019 በቀን 19/02/2010 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 34/2019 በቀን 23/02/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 35/2019 በቀን 26/02/2019 ጨረታ ቁጥር 36/2019 በቀን 30/02/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የምናካሂድ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ እያሳወቅን፣ የዕቃዎችን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ እና ካርጎ ውርስ መጋዘን በመገኘት መመልከት ይቻላል።

  10. በሐራጅ ጨረታ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100.00 (አንድ መቶ) ለየዘርፉ CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOM BRANCH OFFICE ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ለጨረታ የቀረቡት የዕቃዎች ዋጋ ከቫት በፊት የተሰጠ መሆኑን እናሳውቃለን።
  12. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች በተናጠል ሳይሆን ለጨረታው ሰነዱ በተሰጠ ኮድ ቁጥር ብቻ የሚሸጥ መሆኑን እናሳውቃለን።
  13. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. በቅ/ጽ/ቤት ደረጃ እየተካሄደ ያለውን የጨረታ አድማስ ለማስፋት፣ ፈጣን የዕቃዎች ማስወገድ ስራ በማከናወን እና ገቢን በወቅቱ ለመሰብሰብ እንዲቻል ጨረታዎችን በወረቀት አልባ (Online) አሠራር ለማስኬድ ከአክሽን ኢትዮጵያ አ.ማ ጋር ለመሥራት በመታሰቡ ዘወትር ሐሙስ የሚካሄደውን ግልፅ ጨረታ በቀጥታ ሙሉ በሙሉ በአክሽን ኢትዮጵያ አ.ማ በወረቀት አልባ (Online) የሚካሄድ መሆኑን እናሳውቃለን።
  15. የአክሽን ኢትዮጵያ አ.ማ መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር +251905115511 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡- ቦሌ ኤርፖርት በስልክ ቁጥር 011 668 45 37 እና 011 668 41 93 ደውለው ይጠይቁ።

በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Addis Ababa Airport Customs Branch Office is selling confiscated assorted goods—electronics, mobile phones, vehicle spare parts, jewelry, clothing, shoes, and other items—via open and auction bids. Bidders must submit a renewed trade license, taxpayer ID, VAT certificate, and proof of tax payment.
Save Tender