Tender Detail

Tender Details

  • Company Kombolcha Customs Branch (የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
  • Address Ethiopia Kombolcha City, Kembolcha, Ethiopia, Phone: 0116730520
  • Website
  • Deadline11 Oct 2026, 9:50 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100(አንድ መቶ ብር)
  • Bid Securityግልፅ ጨረታ: የመግዣ ዋጋ 5%፤ ሀራጅ: መነሻ ዋጋ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ 200,000 ብር፣ ከ2 ሚሊየን ብር በታች 100,000 ብር (CPO)
  • opening dateማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ስድስተኛው ቀን፤ ግልፅ ጨረታው 3:50 ሰዓት ተዘግቶ 4:00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ሀራጅ ጨረታው 4:30 ሰዓት የሚጀመር ይሆናል
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Electronics Materials , Cloth And Shoes

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ adhesive and modified epoxy risen anchoring፣ የገና አባት ልብስ /santasuit/፣ ፕላስቲክ ሸራ፣ ኮስሞቲክስ፣ ጫማ፣ ሞባይል ቻርጀር፣ አባበር፣የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ አልባሳት እና ሞባይል በግልፅ እንዲሁም ላፕቶፕ፣ አልባሳት እና ኮስሞቲክስ በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Kombolcha Customs Branch (የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)


የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር -09/2019 ዓ.ም

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ adhesive and modified epoxy risen anchoring፣ የገና አባት ልብስ /santasuit/፣ ፕላስቲክ ሸራ፣ ኮስሞቲክስ፣ ጫማ፣ ሞባይል ቻርጀር፣ አባበር፣የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ አልባሳት እና ሞባይል በግልፅ እንዲሁም ላፕቶፕ፣ አልባሳት እና ኮስሞቲክስ በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን መስፈርቶቹ፡-

  1. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ግለሰብ መጫረት ይችላል፡፡
  2. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ግለሰብ መጫረት ይችላል፡፡
  3. የዚህ አንቀፅ ተራ ቁጥር (1) ድንጋጌ ቢኖርም ማንኛዉም ዋጋው ከብር 2 ሚሊየን በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ሰርተፍኬት) ማቅረብ አያስፈልገውም፡፡
  4. በጨረታ የሚሸጠው እቃ በኮሚሽኑ ቁጥጥር ስር ከመግባቱ በፊት ባለቤት የነበረ ወይም የባለቤቱ ወኪል ወይም ቤተሰብ የሆነ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡
  5. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ አይነትና ብዛት የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) እየከፈሉ ኮምቦልቻ ጽ/ቤት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው (6) ቀን 03:00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታው የዕቃዎቹን ዝርዝር በያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝና በፊደል ገልፀው እና በተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለፁትን በኢንቬሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 3:50 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
  7. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ስድስተኛው ቀን በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ፅ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን ግልፅ ጨረታው 3:50 ሰዓት ተዘግቶ 4:00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ሀራጅ ጨረታው 4:30 ሰዓት የሚጀመር ይሆናል፡፡
  8. ተጫራቾች በጨረታዉ አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ05 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በመክፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ከፍለው የማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ እቃው እንደገና ለጨረታ ይቀርባል፡፡
  9. ተጫራቾች ለእቃዎች በሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ አሸናፊ ከሆኑ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ 15% (VAT) የሚጨመርበት ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን ድረስ ለሽያጭ የተዘጋጁ እቃዎችን በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ8:00 ሰዓት እስከ 10:00 ሰዓት ድረስ እና ስድስተኛው ቀን ጧት 3:00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፡፡
  11. ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ እቃዎች የሰጡትን የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና ለሀራጅ ጨረታ የእቃው መነሻ ዋጋ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ለሆነ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 መቶ ሺህ ብር እንዲሁም የእቃው መነሻ ዋጋ ከ 2 ሚሊየን ብር በታች ለሆነ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000 መቶ ሺህ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  12. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 033 551 06 93 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Kombolcha Customs Branch seeks to sell assorted confiscated goods—including adhesives, epoxy anchoring, Santa suits, plastic tarps, cosmetics, shoes, mobile chargers, vehicle spare parts, clothing, mobile phones, and laptops—via open and auction bidding. Bidders must provide a valid trade license, VAT registration, tax clearance, and TIN.
Save Tender