የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባለው በጀት የቢሮ ቦታ ኪራይ ግዥ (Procurement of Rental of secure office space) ግዥ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) (የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- ECMA/NCB/OB/02/2019
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባለው በጀት የቢሮ ቦታ ኪራይ ግዥ (Procurement of Rental of secure office space) ግዥ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል::
በዚሁ መሰረት:-
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን እና ሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመ/ቤታችን አካውንት 1000586364824 ገቢ በማድረግ ከባለስልጣኑ ፋይናንስና ግዥ ክፍል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ፋይናንስ እና ቴክኒካል ኦሪጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸውን በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረገጽ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃቸውን እንዲሁም የተፈረመና ማህተም ያለው የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የተገባበት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
- ተጫራቾች ዋጋቸውን በመሙላት ባለስልጣኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጨረታ መዝጊያ ሰአት በፊት ማስገባት አለባቸው:: ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡና ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ15 ቀናት ብቻ ነው::
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና የተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል ፊርማ መኖር ይገባቸዋል::
- አሸናፊው ተጫራች አገልግሎቱ በተፈለገ ጊዜ አገልግሎቱን የመስጠት ሃላፊነት አለበት::
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበርያነት የብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
- ተጫራቾች የቀረበውን ዝርዝር መስፈርት መሰረት በማድረግ የሚያቀርቡትን አገልግሎት ዝርዝር የቴክኒክ መግለጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል::
- አንዱ ተጫራቾ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም::
- ጨረታው ጥቅምት 9 ቀን 2019 ከሰዓት በ04:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከሰዓት በ4: 30 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
- በጨረታው መክፈቻ ዕለት የተጫራቾች አለመኖር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም::
- ባለስልጣኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ተጨማሪ ማብራርያ ካስፈለገ በአካል የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አድራሻ ቦሌ መንገድ ፍላሚንጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ ባለው ወ/መ/ቤት በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ::
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን
የፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት
ከፍላሚንጎ ሬስቶራንት ወደ አደራ ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ምናዩ ህንፃ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ:- 011-5-57-83-27
ኢሜል:- Procurement@ecma.gov.et
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Capital Market Authority seeks to rent secure office space via national competitive bid. Bidders need a renewed trade license, business registration, VAT registration, TIN, and proof of registration on the government procurement portal, plus a signed anti-fraud declaration.
