Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
  • Address አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-56-98-69
  • Websitehttps://press.et/
  • Deadline10 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price50
  • Bid Security20,000 (ሃያ ሺህ) ብር በሲፒኦ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቢድ ቦንድ
  • opening dateበዚያው ቀን 4:30 ላይ ይከፈታል (እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን)
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በመጋዘን የተጠራቀሙ ጋዜጦችን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል (በድጋሚ የወጣ የንብረት ማስወገድ ጨረታ)

Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)


በድጋሚ የወጣ የንብረት ማስወገድ ጨረታ

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በመጋዘን የተጠራቀሙ ጋዜጦችን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ኮፒ በመያዝ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡

  1. ተጫራቾች ለሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት አንደኛ ፎቅ በሚገኘው አቅርቦት መምሪያ በመምጣት መግዛት ይቻላል፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 20,000 (ሃያ ሺህ) ብር በሲፒኦ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቢድ ቦንድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ኮፒና የሚወዳደሩበትን ዋጋ በአንድ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ6ኛው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከረፋዱ 4:00 ሠዓት ታሽጎ 4:30 ላይ በመሥሪያ ቤቱ አቅርቦት መምሪያ ቢሮ ይከፈታል የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  4. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሑፍ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸናፊበትን ሙሉ ክፍያ ከፍሎ ንብረቶችን ማንሳት ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ባያነሳ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ይወረስበታል፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች በሌላው ላይ ተመስርቶ ዋጋ ማስገባት አይችልም፡፡
  6. ድርጅታችን ጨረታውን አስመልክቶ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0911-08-80-99 ወይም 0913-21-50-37

አድራሻ፡- 4 ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Press Agency seeks to sell newspapers accumulated in its warehouse via competitive bid. Interested bidders must present a copy of valid ID, pay a non-refundable 50 birr for the document, and submit a 20,000 birr bid bond. The winner must pay in full and collect the items within 5 working days.
Save Tender