ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጭነት መኪና ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሸገር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጭነት መኪና ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 007/2019
ድርጅታችን ከጅማ ዞን ከሚገኘው ከጢሮ አፈታ ልዩ ስሙ /አገሎ/ ደን እስከ ፊንፊኔ (አ/አ) ድረስ ደን ውስጥ የተዘጋጀውን የጽድ ግንድ ለማጓጓዝ የጭነት መኪናን በጨረታ አወዳድሮ ለማስጫን ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው፡፡
- በዘርፉ የተሰማራችሁ ሁሉም ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ከፌዴራል/ከክልል/ ትራንስፖርት ባለስልጣን የታደሰ የጭነት አገልግሎት የደረጃ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው እና ኮፒውን ማቅረብ የምችሉ
- የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት (የምስክር ወረቀትና) የታደስ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- ጊዜው ያላለፈበትን በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ነፃ የምስክር ወረቀት (Tax clearance certificate) ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራች ድርጅቶች የቴክኒካልና የፋይናንስ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራች ድርጅቶች የጨረታ ማስከበርያ 200,000.00 በ cpo ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኦርሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሸገር ቅርንጫፍ በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሌላው ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
- ተጫራች ድርጅቶች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ከጨረታው መከፈቻ ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው የጨረታ ሠነዱን ለቡ መብራት ኃይል ሮያል ከረሜላና ቸኮሌት ፋብሪካ ህንጻ 3ተኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው ቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን ከሰኞ እስከ አርብ በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ቅዳሜ እሁድ እና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በዕለቱ ከጠዋቱ በ4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ ይችላል፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0912080221 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሸገር ቅርንጫፍ
✨ messages.ai_summary
Oromia Forest and Wildlife Enterprise, Sheger branch, seeks bidders to transport sawn timber logs by cargo truck from Tiro Afeta (Agaro) forest in Jimma Zone to Finfine (Addis Ababa). Open to licensed transport firms or individuals with renewed freight service competency, tax registration, and valid trade license.
