Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ወረዳ 11 ትምህርት ጽ/ቤት የሶር አምባ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address አዲስ, Phone: 011-8-27-78-01
  • Website
  • Deadline13 Oct 2026, 8:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceየማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ ብር)
  • Bid Securityበሎት: ከብር 450.00 እስከ 10,500.00 (በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ)
  • opening dateተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን
  • Categories Building Materials , Textile, Garment & Leather , Stationery Materials

የሶር አምባ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት አመት የደንብ ልብስ፣ የትምህርት እቃዎች፣ የህትመት ስራዎች፣ የህክምና እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ ጥገና እና የህንፃ ቁሳቁስ (ሎት 01-08) በግልፅ ጨረታ መግዛት/ማሰራት ይፈልጋል

በአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ወረዳ 11 ትምህርት ጽ/ቤት የሶር አምባ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የግልጽ ጨረታ መመርያ

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ስር የሚገኝ የሶር አምባ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት አመት ከዚህ በታችየተዘረዘሩትን -ሎት 01 የመምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች የደንብ ልብስ የስፖርት ትጥቅ፣ሎት 02 የትምህርት እቃዎች፣ ሎት 03 የህትመት ስራዎች ሎት 04 የህክምና እቃዎች ሎት፣05 የፅዳት / ሌሎች አላቂ እቃዎች እና አቅርቦቶች 06 ለፕላንት ለማሽነሪ እና ለመሳሪያ እድሳት እና ጥገና 07 ለህንጻ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች እደሳት እና ጥገና ሎት 08 ለህንፃ ለቁሳቁስና ለተገጣጣሚ መግዣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ማሰራት ይፈልጋል::

  • እያንዳንዱ ተጫራች የሚከተሉትን ነጥቦች በመረዳት የጨረታ ሰነዳቸውን በዚህ መመሪያ መሰረት አሟልተው እንዲያቀርቡ ያስፈልጋል::
  1. ተጫራቾች የዘመኑ ግብር የከፈሉበትንና አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤ ከገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስቴር ወይም በአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡትን የምስክር ወረቀትና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል::በተጨማሪም በኤጀንሲው ድረ-ገጽ/ዌብሳይት/www.ppa.gov.et መገኘት አለባቸው::
  2. የጨረታ ሰነዱ በፖስታ ታሽጎ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሳጥን የሚታሸግበት ሰዓት ከመድረሱ በፊት መግባት ይኖርበታል::
  3. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-8 ከተዘረዘሩት የጨረታ ዓይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ:: በተጨማሪ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር የስራ ሰዓት እስከ 11:30 የጨረታ ሰነድ በሶር አምባ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከፍያ ሂሳብ አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት በመቅረብ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ ብር) ከፍሎ በመውሰድ ከቀኑ 11:30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ::
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ዓይነት ውስጥ የተዘረዘሩትን እቃዎች ያአንዱን እቃ ዋጋ ቫትን ጨምሮ በግልጽ ማስፈር አለባቸው::
  5. ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን አድራሻቸውንና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ የሰነድ ገጽ ላይ በማኖር በማህተም ማረጋገጥ አለባቸው::
  6. በጨረታ አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት ከመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ጋር በሚገባው ውል መሰረት እቃዎቹን እንዲያስገባ ሲታዘዝ በራሱ ወጪ እቃ ግምጃ ቤታችን ድረስ አቅርቦ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት::
  7. ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያነት የሚያገለግል የገንዘብ መጠን በየጨረታ ሎት ተከፋፍሎ እንደሚከተለው ቀርቧል::
    ሎት 01 የመምህራንእና የአስተዳደር ሰራተኞች የደንብ ልብስ በዚህ ክፍል የተጠየቀው የብር መጠን7,500.00 ብር በ 0.5% ተሰልቶ
    ሎት 02 የትምህርት እቃዎች7,590.00 ብር በ 0.5% ተሰልቶ
    ሎት 03 የህትመት ስራዎች2,500.00ብር በ 0.5% ተሰልቶ
    ሎት 04 የህክምና እቃዎች450.00 ብር በ 0.5% ተሰልቶ
    ሎት 05 የፅዳት /ሌሎች አላቂ እቃዎች እና አቅርቦቶች3,250.00 ብር በ 0.5% ተሰልቶ
    ሎት06 ለፕላንት ለማሽነሪ እና ለመሳሪያ እድሳት እና ጥገና3,750.00 ብር በ 0.5% ተሰልቶ
    ሎት 07 ለህንጻ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች እደሳት እና ጥገና4,000.00 ብር በ 0.5% ተሰልቶ
    ሎት 08 ለህንፃ ለቁሳቁስና ለተገጣጣሚ10,500.00ብር በ 0.5% ተሰልቶ
    መሆኑን አውቃቹ ተጫራቾች ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቬሎፕ አሽጎ በጨረታ ሳጥን ውስጥ በመስሪያ ቤታችን ስም ማሲያዝ ይኖርባቸዋል::በተጨማሪም የጨረታ ሰነዱን የሚሞላ ከፍል በአግባቡ ሞልቶ ተመላሽ ያላደረገ አቅራቢ ከጨረታ እንደሚሰረዝ እናሳስባለን::
  8. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች በዚህ ጨረታ እንዲወዳደሩ እየተጋበዙ እንዲሁም ከደራጃቸው አካል ለጨረታ ሰነድ ማሻር በጨረታ ማስከበሪያነት የሚያገለግል በመስሪያ ቤቱ ስምና ሀላፊነት መውሰድ በሚችል አካል የተፃፈ ደብዳቤ እና አምራች መሆናቸው የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::ይህንን ማቅረብ ካልቻሉ እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይገዛሉ የጨረታና የውል ማስከበሪያ ያሲዛሉ::
  9. የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም ::
  10. ጨረታው ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በሚቀጥለው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 ላይ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል:: ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ እቃ ከጨረታው መዝጊያ ሰአት ከሁለት ቀን በፊት ናሙናዎችን ማቅረብና ለግዥ (ለተወከለው) ሰራተኛ ማስረከብ ይኖርበታል ::ናሙና ማቅረብ የማይቻልባቸው ቋሚ እቃዎችን በፎቶ በማስደገፍና ስለ እቃው አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ማቅረብ አለባቸው::
  11. የመ/ቤቱ የእቃ ጥራት ተቆጣጣሪ ኮሚቴ(የቴክኒክ ኮሚቴ)ያቀረቡትን የእቃዎቹን ጥራት አይቶ ከመስሪያ ቤቱ ፍላጎት ጋር የማይጣጣም ነው ብሎ ካመነ ዕቃው እንዲመለስ ማድረግ ይችላል::
  12. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት/ድርጅቶች ማሸነፋ እንደተገለፀለት በተሰጠው የጊዜ ገደብ ከ7ኛው-15ኛው ቀን ውስጥ ቀርቦ ውል ካልፈፀመ በጨረታ ማስከበሪያነት ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ መ/ቤቱ እንደ ምርጫው ሁለተኛው ወይም ሶስተኛው የወጣውን ተወዳዳሪ ሊጋብዝ ይችላል::
  13. የግዥ ውል በሚፈፀምበት ጊዜ ለውል ማስከበሪያነት የሚውል ያሸነፉትን እቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
  14. የግዥ ውል በሚፈፀምበት ጊዜ መ/ቤቱ በጨረታ ሰነድ ላይ የተመለከተውን የእቃ ብዛትና ተያያዥ አገልግሎቶች እስከ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል::
  15. ለቋሚ እቃዎች እና የማሽን ቀለሞች ትክክለኛ ለመሆናቸው አሸናፊ ተጫራቾች ለአንድ አመት ዋስትና ይሰጣል::
  16. መ/ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በድርጅቱ የስራ ቦታ በመገኘት የእቃዎችን ጥራትና የድርጅቱን አቅም ለመገምገም ቢፈልግ ድርጅቱ የመተባበር ግዴታ አለበት::
  17. ለውድድር የሚቀርበው የጨረታ ሰነድ ኮፒ ከኦርጅናል ሰነድ ጋር ለየብቻ ማቅረብ ይኖርበታል:: በተጨማሪም ተጫራቹ የገዛው ሙሉ ሰነድ ኮፒ እና ኦርጅናል ሙሉ በሙሉ ተመላሽ ካላደረገ ከጨረታ ውጭ ይሆናል::
  18. በመ/ቤታችን ለእቃ ጥራት ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ በመሆኑ ተወዳዳሪዎች የተሻለ ጥራት ያላቸውን እቃዎች እንዲያቀርቡ ይበረታታሉ::
  19. ለማጭበርበር የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል::
  20. የእቃውን ዋጋ ማቅረብ የምትችሉት ት/ቤቱ በሸጠላቹ ሰነድ ብቻ ሞልታቹ ማቅረብ አለባችሁ::
  21. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ :-ከአጠና ተራ ሎሚ ሜዳ ሲደርሱ ወደ ግራ 200 ሜትር ገባ ብሎ ኢንደስትሪ መንደር አካባቢ የሚገኘው የሶርአምባ የመ/ደ/ት/ቤት

አዲስ አበባ አዲስ ከተማ
ስልክ ቁጥር 011-8-27-78-01

የሶር አምባ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Soor Amba Primary and Middle School seeks suppliers for Lot 01–08: uniforms and sports gear, educational materials, printing, medical supplies, cleaning/consumables, plant and machinery repair, and building materials. Bidders may bid for all or some lots. Requirements include a valid trade licence, VAT registration, and samples.
Save Tender