Tender Detail

Tender Details

  • Company ሐረር ብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ.
  • Address ሀረር ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 025-666-4078
  • Website
  • Deadline17 Oct 2026, 9:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityየአንድ ካሬ ዋጋ × 800 ካሬ ጠቅላላ ዋጋ 1% (CPO ወይም ባንክ ገቢ)
  • opening dateበ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:30 በዋናው መስሪያ ቤት ይከፈታል
  • Categories Accounting & Auditing , Audit Service

የሐረር ብድርና ቁጠባ ተቋም አ/ማህበር ከ2026 GC እስከ 2028 GC ድረስ ያሉትን የበጀት ዓመት የፋይናንስ ሰነዶቹንና የሒሳብ መግለጫዎቹን የፐብሊክ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል።

ሐረር ብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ.


(PUBLIC AUDITOR) ቅጥር የጨረታ ማስታወቂያ

የሐረር ብድርና ቁጠባ ተቋም አ/ማህበር ከ2026 GC እስከ 2028 GC ድረስ ያሉትን የበጀት ዓመት የፋይናንስ ሰነዶቹንና የሒሳብ መግለጫዎቹን የፐብሊክ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል። ስለሆነም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ (NBE) መመሪያዎች እና በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ (AABE) መስፈርቶች መሰረት ብቁ የሆነ የኦዲት ድርጅት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ MFI 037/2024 መሰረት ተወዳዳሪዎች ማሟላት የሚገባቸው ዋና ዋና መስፈርቶች:-

  1. የታደሰ የሙያ ፈቃድ፤
  2. በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ (AABE) የተሰጠ የስነ-ምግባር ጉድለት የሌለበት መሆኑን የሚያሳይ ደብዳቤ፤
  3. የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የግብር ክሊራንስ (clearance) የምስክር ወረቀት ማቅረብ፤
  5. የባንክ ወይም የፋይናንስ ተቋማትን ኦዲት ማድረግ ላይ የ3 አመት የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችል፤
  6. የእያንዳንዱ የኦዲተር አባላት (ሰራተኞች) የነጻነት ማረጋገጫ (Independence Confirmation as per Annex i)
  7. የእያንዳንዱ የኦዲተሩ አባላት ለስራው ብቁ መሆናቸውን የሚያሳይ ማረጋገጫ (according to Directive Annex ii)
  8. የኦዲተሩ ድርጅት አባላት በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ደረጃዎች (IFRS) መሰረት የፋይናንስ ተቋማትን ኦዲት ማድረግ ላይ እውቀት እና የስራ ልምድ ያላቸው መሆኑን የሚገልጽ የተፈረመበት CV ማቅረብ የሚችል፤
  9. የእያንዳንዱ የኦዲተር አባላት (ሰራተኞች) መልካም ስነ-ምግባር ማረጋገጫ ወረቀት ከፖሊስ ጣቢያ ማቅረብ የሚችል፤
  10. የእያንዳንዱ የኦዲተር አባላት (ሰራተኞች) የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት፤
  11. በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ደረጃዎች (IFRS) እና Association of chartered certified Accountants (ACCA) መሰረት የእያንዳንዱ የኦዲተሩ አባላት የባንክ ወይም የማይክሮ ፋይናንስ ሂሳብ ኦዲት የማድረግ ስልጠና የወሰዱ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል።

ተወዳዳሪዎች ኦዲቱ ለሚከናወንበት የ3 አመት አጠቃላይ ክፍያ ስንት እንደሆነ መጥቀስ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ክፍያው የሚፈጸመው አሸናፊው ኦዲተር ያቀረበው አጠቃላይ ክፍያ ለ3 ከተካፈለ በኋላ በእያንዳንዱ የስራ አፈጻጸም ይሆናል።

የሰነድ አቀራረብና የጨረታ ሂደት

ተወዳዳሪዎች የቴክኒክ (Technical) እና የፋይናንስ (Financial) ፕሮፖዛሎቻቸውን በተዘጋጁ ሁለት የተለያዩ በታሸጉ ኤንቨሎፖች ማቅረብ አለባቸው።

ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው የስራ ቀን በዋናው መስሪያ ቤት ከጠዋቱ 3:30 ተዘግቶ 4:30 ይከፈታል።

ጨረታው በዕለቱ እና በሰዓቱ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

አድራሻ:- ሐረር ከተማ ጅንኤላ ወረዳ ቀበሌ 14 ኦሬንታል ፎቶ ቤት የሚገኝበት ህንጻ ወይም የሐረር ክልል ጠቅላይ ዓ/ህግ ቢሮ ፊት ለፊት በሚገኘው የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት የሰው ሃብት ክፍል።

የሐረር ብድርና ቁጠባ ተቋም አ/ማህበር

✨ messages.ai_summary
Harar Credit and Savings Institution seeks a qualified audit firm for public audit of its financial documents and statements for three budget years. Bidders must meet NBE and AABE requirements, hold valid licenses, TIN, tax clearance, 3 years' bank/MFI audit experience, and submit staff independence and qualification evidence.
Save Tender