Tender Detail

Tender Details

  • Company ካፒታል ኃ/የተ/መሰ/የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር
  • Address Addis Ababa, Phone: 0952285009
  • Website
  • Deadline05 Oct 2026, 5:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት ውስጥ
  • Categories Accounting & Auditing , Audit Service

ካፒታል የቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር (Capital Saving and Credit Cooperative) በውጭ ኦዲተሮች አወዳድሮ ማስመርመር ይፈልጋል።

ካፒታል ኃ/የተ/መሰ/የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር


ለኦዲት አገልግሎት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ካፒታል የቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር (Capital Saving and Credit Cooperative) ህጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት ሲሆን፣ በ 'Peachtree Accounting' ሶፍትዌር የተመዘገበውን ከመጋቢት 01/2016 እስከ ሰኔ 30/2018 ያለውን ሂሳብ መረጃ ወደ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ደረጃዎች (International Financial Reporting Standards - IFRS) በማስቀየር (convert በማስደረግ) በውጭ ኦዲተሮች አወዳድሮ ማስመርመር ይፈልጋል።

ስለሆነም፤ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ የኦዲት ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ እንጋብዛለን::

ተወዳዳሪዎች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች:-

  1. የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው።
  2. የታክስ ማስረጃ፣ የከፍያ ታክስ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ያለው፤ እንዲሁም በቅርብ ጊዜ የተሰጠ የታክስ ክሊራንስ (Tax Clearance) ማቅረብ የሚችል።
  3. የሙያ ብቃት ማረጋገጫ በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ (AABE - Accounting and Auditing Board of Ethiopia) የተሰጠ የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያለው።
  4. የስራ ልምድ፣
    • በፋይናንስ ተቋማት፤ በተለይም በቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት ላይ በኦዲት ስራ በቂ ልምድ ያለው።
    • በ 'Peachtree' ሶፍትዌር የተመዘገበ የሂሳብ መረጃን በማፅዳት ወደ IFRS ስርዓት የመቀየር (IFRS Conversion) እና ይህንኑ ደረጃ ያሟላ የፋይናንስ ሪፖርት የማዘጋጀት በተግባር የተደገፈ ልምድ ያለው።

የጨረታው ሁኔታ እና መመሪያ

  • ተወዳዳሪዎች የቴክኒክ እና የፋይናንስ ሰነዶቻቸውን (Technical and Financial Proposal) በታሸገ ኤንቨሎፕ እና በድርጅቱ ማህተም በማስደገፍ ማቅረብ አለባቸው።
  • የማቅረቢያ ቦታ:- አዲስ አበባ፣ ቦሌ አትላስ፣ አዲስ ሴንቼሪ ሪል እስቴት፣ 8ኛ ፎቅ።
  • የምዝገባ ጊዜ:- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት ውስጥ።

የማህበሩ መብት:-

  • ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ:-

  • ለበለጠ መረጃ: ስልክ ቁጥር 0909535479 / 0952285009 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ::

ካፒታል ኃላ/የተ/መሰረታዊ የቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር

✨ messages.ai_summary
Capital Saving and Credit Cooperative seeks external auditors to convert its Peachtree-recorded accounts to IFRS and audit them. Bidders must hold a valid business license, TIN, VAT registration, recent tax clearance, and a renewed AABE professional competency certificate, plus proven audit experience with SACCOs and IFRS conversion.
Not stated in the notice: bid security, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender