Tender Detail

Tender Details

  • Company የዶ/ር ደስታ ላንገና ፋውንዴሽን
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline02 Oct 2026, 5:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የሥራ ቀናት
  • Categories Accounting & Auditing , Audit Service

የውጭ ኦዲተር የጨረታ ጥሪ (ለሁለተኛ ጊዜ) - የ2016፣ 2017 እና 2018 ዓ.ም. የፋይናንስ ሪፖርቶች ኦዲት - የዶ/ር ደስታ ላንገና ፋውንዴሽን

የዶ/ር ደስታ ላንገና ፋውንዴሽን


ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የውጭ ኦዲተር የጨረታ ጥሪ

የዶ/ር ደስታ ላንገና ፋውንዴሽን የ2016፣ 2017 እና 2018 ዓ.ም. የበጀት ዓመታት የፋውንዴሽኑን የፋይናንስ ሪፖርቶችና የሒሳብ መግለጫዎች በገለልተኛ የውጭ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች የድርጅታቸውን መግለጫ፣ የሕጋዊ ምዝገባና የሙያ ፈቃድ፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ አስፈላጊውን የግብር ማረጋገጫ፣ በተመሳሳይ የኦዲት ሥራ ያላቸውን ልምድ የሚያረጋግጡ ሰነዶችን እንዲሁም የሙያ ብቃት መረጃ ማቅረብ አለባቸው። በተጨማሪም የኦዲት ሥራውን አፈጻጸም የሚያብራራ የቴክኒክ ፕሮፖዛል፣ የኦዲት ክፍያን የሚያሳይ የፋይናንስ ፕሮፖዛል፣ የሥራ ዕቅድና የሥራውን የማጠናቀቂያ ጊዜ የሚገልጽ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች የሚፈለጉትን ሰነዶች በማሟላት የቴክኒክና የፋይናንስ ፕሮፖዛሎቻቸውን በታሸገ ሁኔታ በዱራሜ ከተማ ለሚገኘው ለዶ/ር ደስታ ላንገናፋውንዴሽን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የሥራ ቀናት በፖስታ ሳጥን ኮድ IARufN/ 0913236083 አድራሻ እንድታቀርቡ እናሳውቃለን።

ለተጨማሪ መረጃ በ 0916276399 ወይም በኢሜይል አድራሻ eyudesta27@gmail.com ማግኘት ይቻላል። ከተገለጸው የመጨረሻ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ ፕሮፖዛሎች ተቀባይነት አይኖራቸውም። የተመረጠው ኦዲተር የኦዲት ሥራውን ከውል በኋላ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ ማጠናቀቅ ይጠበቅበታል።

ፋውንዴሽኑ የቀረቡትን ፕሮፖዛሎች በተቀመጡ መስፈርቶች መሠረት የመገምገምና ተገቢውን ኦዲተር የመምረጥ መብቱን የጠበቀ ሲሆን፣ ማንኛውንም ፕሮፖዛል በሙሉ ወይም በከፊል የመቀበል ወይም ያለመቀበል መብቱም የተጠበቀ ነው።

የኦዲት ሥራው ወሰን

የተመረጠው የውጭ ኦዲተር የፋውንዴሽኑን የፋይናንስ ሪፖርቶች፣ የገቢና ወጪ ሂሳቦች፣ የባንክ ሂሳቦች፣ እንዲሁም ተያያዥ የሒሳብ መዝገቦችና የፋይናንስ ሰነዶችን በተፈጻሚው የኦዲት ስታንዳርድ መሠረት በመመርመር የፋይናንስ ሪፖርቶቹ ትክክለኛነትና ተገቢነት ላይ የኦዲት አስተያየት ይሰጣል። ኦዲቱን ከጨረሰ በኋላ የኦዲት ሪፖርት የሚያቀርብ ሲሆን፣ በኦዲቱ ወቅት የታዩ የፋይናንስ አሠራር፣ የውስጥ ቁጥጥር ወይም ሌሎች የማሻሻያ ጉዳዮች ካሉ ተገቢውን የማሻሻያ ምክረ ሃሳብ ያቀርባል።

የዶ/ር ደስታ ላንገና ፋውንዴሽን

✨ messages.ai_summary
Dr. Dessta Langena Foundation seeks an independent external auditor to audit its financial reports and statements for three budget years, covering income/expenditure, bank accounts, and related records, with an audit opinion and improvement recommendations. Bidders must submit company profile, legal registration, professional license, renewed business license, tax clearance, and relevant audit experience.
Not stated in the notice: bid security, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender