የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የደንብ ልብስ፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ ቋሚና አላቂ ዕቃዎች፣ የስፖርትና የቤተሙከራ እቃዎች ግዥ
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
| ሎት | የእቃው /የስራው ዓይነት | ከአጠቃላይ በጀት የተወሰደው መጠን በ% | ለየሎቱ የሚያስይዘው ማስከበሪያ /CPO/ መጠን |
| 1 | የደንብ ልብስ | 0.5 | 9500.00 |
| 2 | የደንብ ልብስ ስፌት | 0.5 | 3500.00 |
| 3 | አላቂ የቢሮና የጽዳት እቃዎች | 0.5 | 5000.00 |
| 4 | የጽህፈት መሳሪያ | 0.5 | 5000.00 |
| 5 | አላቂ ዕቃዎች | 0.5 | 3500.00 |
| 6 | ቋሚ እቃዎች | 0.5 | 10000.00 |
| 7 | የስፖርት እቃዎች | 1 | 5000.00 |
| 8 | የተለያዩ ጥገናዎች | 1 | 5000.00 |
| 9 | የቤተሙከራ እቃዎች | 0.5 | 4500.00 |
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል::
- ተጫራቾች የንግድ ፍቃዳቸው Online የተመዘገበ መሆን አለበት::
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ - ናሙና (ሳምፕል)ለሚፈለግባቸው ዕቃዎች ማቅረብ የሚችሉ-
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ ማስረጃ የሚያቀርቡ - የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው
- በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 2 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸውን ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ 7/ሰባት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ባሸነፉባቸው ዕቃዎች ላይ _10%(ፐርሰንት) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝና ተዋውለው እቃዎቹን ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በዝዙት ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ(ቫት) ጨምሮ በመግለፅ ዋናውን እና ኮፒውን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ ላይ በተጠቀሰው የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 2 ለዚሁ ተብሎ ለተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ አካላት ሲሆኑ ሰነድ ለመውሰድ በሚመጡበት ወቅት ከሚመለከተው አካል ወቅቱን የጠበቀ በፅህፈት ቤቱ ስም የተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: በተጨማሪም መወዳደር የሚችሉት በራሳቸው በተመረተ ምርት ብቻ ይሆናል::
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2:30-10:00 ሰዓት ድረስ በየካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመገኘት የማይመለስ ብር 400.00/አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም
- ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ለ10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛ ቀን በ3:00/ሶስት/ ሰዓት ታሽጎ በ3:30/ሶስት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ/ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
- ተጫራቾች የዝዘቻሁትን ሙሉ ሰነድ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር አብራችሁ ማስገባት አለባችሁ:: ሙሉ ሰነዱን ያላስገባ ተጫሪች ከውድድር ውጪ ይደረጋል::
- የግዥ ውል በሚፈፀምበት ወቅት መ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተመለከተው የዕቃ ብዛት እስከ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0112768120/0112303241/0112303054 በመደወል መጠየቅ ይቻላል::
አድራሻ:- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አውቶብስ ተራ ወደ መሳለሚያ በሚወስደው መንገድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮልፌ
የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
✨ messages.ai_summary
The school seeks to buy uniforms, tailoring services, consumable office and cleaning supplies, stationery, fixed assets, sports and laboratory equipment, plus various repairs. Bidders need an online-registered trade licence, renewed sector licence, tax compliance, VAT registration, TIN, and samples where required.
