የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለብድር ገንዘብ ማካካሻነት በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከበውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የመያዣ ንብረቶች በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Development Bank(የኢትዮጵያ ልማት ባንክ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለብድር ገንዘብ ማካካሻነት በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከበውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የመያዣ ንብረቶች በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
| ተ.ቁ | የተበዳሪው/ የመያዣ ሰጪው ስም | የንብረት አድራሻ | የንብረት ዝርዝር | የቦታ ስፋት (በሄክታር) | የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር | የጨረታ ሁኔታ | የጨረታ ደረጃ | ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
| ማጃንግ እግሮ ኢንዱስትሪ ማህበር | ጋምቤላ ህ/ብ/ህ ወረዳ፣ አሽኔና ባያ ቀበሌ | የመስኖ እርሻ እና ግንባታዎች፡ የእርሻ ማሽነሪዎች፣ ተሽከርካሪዎች 199.33 ሄክታር ላይ የተተከለ የመዝ ቋሚ ተክል ያለው | 1000 ሄክታር | 393.239.093.239,016.73 | ድርድር | የመጀመሪያ | ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00-6:00 ሰዓት | |
| ኤም ዋይ ሹዝ ኤንድ ሌዜር ማኑፋቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማ | አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደብረ ብርሃን ከተማ 09 ቀበሌ | የጫማ እና የቆዳ ማምረቻ ፋብሪካ (በትግበራ ላይ ያለ) የህንፃ ግንባታዎች፣ ማሽነሪዎች እና የኤልከትሪክ ሥራዎች | 6.83 ሄክታር | 457.236.714.80 | ዝግ | ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00-6:00 ሰዓት |
ማሳሰቢያ፤
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በፎርማቱ ላይ በመጥቀስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ሁለተኛ ታወር ምድር ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ ከሦስተኛው ቀን ጀምሮ ከማጃንግ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግል ማህበር የተረከበውን ንብረት ለመግዛት እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ድረስ እንዲሁም ከኤም ዋይ ሹዝ ኤንድ ሌዜር ማኑፋቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተረከበውን ንብረት ለመግዛት እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡50 ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ከፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰንጠረዡ በተመለከተው ቀንና ሰዓት በባንኩ ዋናው መ/ቤት ይካሄዳል፡፡ ህጋዊ ሰውነት ያለው አካላት ወኪል በጨረታው ለመሳተፍ የሚቀርብ ሰው የማህበሩን መመስረቻ ፅሁፍ/መተዳደሪያ ደንብ ከእነማሻሻዎቹ ካሉ፤ የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፈቃድ፣ ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችን እና የተረጋገጠ የውክልና ስልጣን ሰነዶችን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ከፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ከፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል፡፡
- እንዳንድ እጉዳንድ የድርጅቱ ንብረቶች የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ስለሆኑ ገዢው የቀረጥ ነጻ መበት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመከፈል ይገደዳል፡፡
- የማጃንግ እግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግል ማህበር የስራ እንቅስቃሴ ያልተቋረጠ በመሆኑ አሸናፊው ከግዢው ዋጋ በተጨማሪ ያልተሰበሰበ ወይም በከምችት ላይ ያለ የሙዝ ምርት በርክክብ ወቅት በሚደረስበት የትመና ዋጋ መሰረት በጥሬ ገንዘብ መግዛት ይችላል፣
- የንብረቱ ስመ ንብረት ለገዥው እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል፡፡ ገዥው ጉዳዩን ተከታትሎ ያስፈፅማል፡፡
- ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው ከተቻለ ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ሲሆን እሸናፊው በባንኩ ብድር ፖሊሲና የአሰራር ስርዓት መሰረት አስፈላጊውን የብድር መስፈርቶች ካሟላና ፕሮጀክቱን የሚያስቀጥል ከሆነ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ማጃንግ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግል ማህበር ቋሚ ሰራተኞች በሙሉ ከመበትና ጥቅማቸው ጋር መረከብ ይጠበቅበታል፡፡
- በጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው፡፡
- በጨረታው ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦንጎይንግ ኮንሰርን ፕሮጀክትስ እና አኳየርድ አሴትስ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-524-53-73/ 011-524-42-69 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡ የመያዣ ንብረቶቹን መጐብኘት የሚፈልግ ከዳይሬክቶሬቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Development Bank seeks to sell repossessed collateral assets via negotiation auction, including an irrigated banana farm with machinery and vehicles, and a shoe/leather factory with buildings and equipment. Bidders must pay a non-refundable fee, submit documents, and deposit 10% of the starting price via CPO.
