Tender Detail

Tender Details

  • Company ዘ ዩዝ ፕሪንት
  • Address Addis Ababa, Phone:
  • Website
  • Deadline01 Oct 2026, 5:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት
  • Categories Accounting & Auditing , Audit Service

ዘ ዩዝ ፕሪንት (The Youth Print) በኢትዮጵያ ውስጥ የተመዘገበ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ሲሆን አገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ግቦች ላይ እየሰራ ይገኛል፡፡

ዘ ዩዝ ፕሪንት


በድጋሚ የወጣ የኦዲት አገልግሎት ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር: TYP/002257/19/26

ዘ ዩዝ ፕሪንት (The Youth Print) በኢትዮጵያ ውስጥ የተመዘገበ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ሲሆን አገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ግቦች ላይ እየሰራ ይገኛል፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 2030 ዘላቂ የልማት ግቦች (SDGs) እና በአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ለማሳካት አዳዲስ የወጣቶች ሃሳቦችን እና ፕሮጀከቶችን በትምህርት፣ በምርምር፣ በፖሊሲ ትንተና፣ ትርጉም ያለው ውይይት እና ዓለም አቀፍ ትብብርን በመፍጠር ላይ እንዲሁም በመደገፍ ላይ ይገኛል፡፡

ድርጅቱ የ2018 ዓ.ም የአንድ ዓመት ሂሳብ በታወቀ B እና ከዚያ በላይ ደረጃ ባለው ፐብሊክ ኦዲት ድርጅት ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ሥራውን ለማከናወን የሚጠይቁትን የገንዘብ መጠንና ሥራውን ለማጠናቀቅ የሚፈጅባቸውን ጊዜ በመጥቀስ፣ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት ከታች በተገለጸው አድራሻ መሠረት በፖስታ አሽገው በማስገባት መወዳደር ይችላሉ፡፡

የኦዲት ድርጅቶቹ የሚከተሉትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው፡፡

  1. አዲተሩ የሙያ ማረጋገጫ ያለው መሆኑ፣
  2. የንግድ ፈቃድ ያለው መሆኑ፣
  3. የዘመኑን ግብር ስለመከፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆኑ፣
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው መሆኑ፣
  5. ከፌዴራል ወይም ከክልል ኦዲተር መሥሪያ ቤት ለበጀት ዓመቱ የታደሰ ፈቃድ ያለው መሆኑ፡፡

አድራሻ፡- አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ ቦሌ ክ/ከተማ ወርዳ 03 H.NO (ሃያት ሆስፒታል ጀርባ)

ለበለጠ መረጃ፦ በስልክ ቁጥር 0947396499/0936114195 መደወል ይቻላል፡፡

Email: theyouthprintet@gmail.com | secretariat@theyouthprint.org

ዘ ዩዝ ፕሪንት

✨ messages.ai_summary
The Youth Print, an Ethiopian civil society organization, seeks a licensed public audit firm at Grade B or above to audit its one-year accounts. Bidders must provide professional certification, business license, tax compliance proof, TIN, and a renewed audit license.
Not stated in the notice: bid security, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender