በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞኑ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ማለትም ሎት1.
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጌዴኦ ዞን የገደብ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞኑ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ማለትም ሎት1. የጽዳት ዕቃዎች ሎት2. ካሜራ እና መለዋወጫዎች ሎት 3. ሞተር ሳይክል ሎት 4. በአከባቢ ማቴሪያል ሆኖ በዘመናዊ ማሽን የሚሰሩ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፣
- በዘመኑ የታደሰ የዘርፉ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል ያለው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
ከላይ በዝርዝር የተቀመጠዉን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፣ ቫትን ያላካተተ ከሆነ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ፤
- ሎት1. የጽዳት ዕቃዎች ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/
- ሎት2. ካሜራ እና መለዋወጫዎች ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/
- ሎት 3. ሞተር ሳይክል ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/
- ሎት 4. በአከባቢ ማቴሪያል ሆኖ በዘመናዊ ማሽን የሚሰሩ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ፈርኒቸር ብር 70,000 /ሰባ ሺህ ብር/ ሲፒኦ እና በባንክ ዋስትና ሆኖ በጥሬ ገንዘብ ብቻ ዋስትና ማቅረብ
ተጫራቾች ዕቃዎች የሚሸጡበትን ዋጋ በተዘጋጀው ዝርዝር ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው አንድ ኦርጅናል ሰነድ እና ሁለት ኮፒ ሰነድ በተለያየ ፖስታ ካሸጉ በኋላ ከሲፒኦ ጋር በአንድ ትልቅ ፖስታ በሰም በማሸግ ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
ኦርጅናልና ኮፒ ሰነድ ላይ ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ /በፍሉድ/ የተስተካከለ በሚታይ መልኩ በድጋሚ ተጽፎ በተጫራች ወይም በህጋዊ ተወካይ መፈረም አለበት፤
በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ የድርጅት ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት፤
ጨረታዉ የሚከፈተዉ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት በተከታታይ በሚቆጠር 15 ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ጠዋት የጨረታው ሳጥን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች በዕለቱ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሠዓት ባለው ጊዜ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታዉ የሚከፈት ይሆናል፡፡
የጨረታው ሳጥን የሚገኘው በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ቅጥር ግቢ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ተወዳድረው ያሸነፉበትን ዕቃዎች ጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ የማጓጓዣ፣ የማስጫኛ እና የማውረጃ ወጪ ችለው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የሚቀርበው የጨረታ ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን በኋላ ለ3 ወር ማለትም ለ90 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0461310108 መደወል ይችላሉ፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ
