Tender Detail

Tender Details

  • Company በቄለም ወለጋ ዞን የየማሎጊ ወለል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ቄለምወለጋዞን የማሎጊ ወለል ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ተጆ : ኦሮሚያ ክልል : ኢትዮጵያ, Phone: 09-10-31-08-20
  • Website
  • Deadline01 Oct 2026, 5:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200 (ሁለት መቶ ብር) በማይመለስ
  • Bid Security10000 (አሥር ሺህ) ብር ሲፒኦ
  • opening dateበማግስቱ ከጠዋቱ 2፡30
  • Categories Furniture And Furnishing , Office Supplies And Services , Stationery Materials

በቄለም ወለጋ ዞን የየማሎሚ ወለል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ/ም በጀት በወረደው ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን እንዲሁም የደንብ ልብስ ለመግዛት የወጣ የጨረታ ደንብ እና መመሪያ እንደሚከተለው ተዘርዝሯል፡፡

በቄለም ወለጋ ዞን የየማሎጊ ወለል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በቄለም ወለጋ ዞን የየማሎሚ ወለል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ/ም በጀት በወረደው ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን እንዲሁም የደንብ ልብስ ለመግዛት የወጣ የጨረታ ደንብ እና መመሪያ እንደሚከተለው ተዘርዝሯል፡፡

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የ2018 የመንግስት ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም /ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. በ/ገ/አ/ት/ሚንስቴር ባቅራቢዎች የተመዘገቡና የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ተካፋይ ለመሆን የሚፈልጉት ዕቃ በምን በምን አይነት እቃዎች ላይ መሆኑን ለይተው መግለፅ አለባቸው፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውንም ሁኔታዎችን መለወጥ ወይም ማሻሻል ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይቻልም፡፡
  6. መስሪያ ቤቱ የሚገዛውን እቃዎች ብዛት እንደአስፈላጊነታቸው በሙሉ ወይም በከፊል ማዘዝ ይችላል፡፡
  7. የሚቀርቡት እቃዎች በተሰጠው እስፕስፊኬሽን ካልቀረቡና ማንኛውም አይነት ስህተት ቢፈፀም ሃላፊነቱ የአቅራቢው ይሆናል፡፡
  8. ጨረታው የሚካሄደው የድርጅቱን የገብያ ጥናት ማእከል የማድረግ ሲሆን ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች አይነት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቹ ያንዱን ዕቃ ዋጋ በቁጥርና በፊደል መፃፍ አለበት፡፡ በቁጥርና በፊደል በተፃፈ መካከል ልዩነት ቢኖር በፊደል የተጻፈው ይወሰዳል፡፡
  9. አቅራቢው ድርጅት እቃዎችን ቄለም ወለጋ ዞን በየማሎጊ ወለል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መጋዝን ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  10. ተጫራቾች ላሸነፉባቸው እቃዎች ከመስሪያቤቱ ጋር ውል መግባት አለባቸው፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ 10000 (አሥር ሺህ) ብር ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  12. አሸናፊዎች በሚገቡት ውል መሰረት ለመፈጸም ለውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ላይ10% በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ለውል ማስከበሪያ የተያዘ ሲፒኦ በውሉ መሰረት እስኪፈጸም ተይዞ ይቆያል፡፡
  13. ከዚህ በላይ በተገለጸው መሰረት ተጫራቾች ውሉን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ ለውል ስምምነት ያስያዙት ገንዘብ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  14. ተጫራቾች በሰነዳቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ገልጸው መፈረም አለባቸው፡፡
  15. የሚቀርበው ሰነድ ስሪዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ የሚታይ መሆን አለበት፡፡
  16. ከተጠየቀው ብዛት እሳንሶ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  17. ተጫራቾች ከጨረታው መከፈቻ እለት ጀምሮ ያቀረቡት ዋጋ የሚቆይበት ጊዜ አጠናቀውሃ validity date/ እቃውን የሚያስገቡበትን ቀን መግለፅ አለባቸው፡፡
  18. አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  19. ተጫራች መሸነፋቸው እንደተረጋገጠ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያው ይመለስላቸዋል፡፡
  20. ተጫራቾች ከሽያጭ በኃላ የሚሰጡት አገልግሎት/after sales service/ ለፅ ይኖርባቸዋል፡፡
  21. ዋጋው መሞላት ያለበት መ ቤቱ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ ብቻ ነው፡፡
  22. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ 21 ተከታታይ ቀናቶች እየር ላይውሎ በዝሁ ቀን በ11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በማግስቱ ከጠዋቱ 2፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  23. በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የጨረታ ሰነድ በማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር ) ከየማሎጊ ወለል ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት መግዛት ይችላል፡፡
  24. ተጫራቾች የቴከኒከና የዋጋ ፖስታ እንድሁም ኮፒ ለየብቻ ወይም በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማሸግ አራቱን በአንድ ላይ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  25. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ዋጋ ቫትን ጨምሮ ማቅረብ አለበት፡፡ወይም የሚያቀርበው ዋጋው ከቫት ጋር መሆን አለበት፡፡
  26. ማንኛውም ተጫራች መ/ቤቱ የፈለጋቸውን ዕቃ ያንዱን ዋጋ መሙላት አለበት፡፡ ሞልቶ ካልተገኘ የሌላ ተጫራች ትልቁ ዋጋ ይደመርበታል፡፡ጨረታው የሚገመገመው የመ/ቤቱ የገበያ ጥናትን ማዕከል ያደረገ ሲሆን ከገበያ ጥናቱ 10 ከፍ ያለ ዋጋ ወይንም ዝቅ ያለ ዋጋ ውድቅ ይደረግና የገበያው የዕቃው የተጠና ዋጋ ይደመርበታል፡፡
  27. በቄለም ወለጋ ዞን የየማሎሚ ወለል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ተጆ ከተማ የጨረታው ሰነድ ስለሚገኝ መጥቶ መግዛት ይቻላል፡፡

ማሳስቢያ: የመ/ቤታችን የግዥ መጠን በ20/% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡ መ ቤታችን የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡

አድራሻ፡- ቁለም ወለጋዞን የማሎጊ ወለል ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ተጆ

ስልክቁጥር፡- 0910310820/0917369084

ተጫራቾች መሸነፋቸው እንደተረጋገጠ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያው ይመለስላቸዋ፡፡

ቄስም ወስጋ ዞን የየማሎጊ ወስስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Supply of durable and consumable office items and uniforms for sector offices in Yemalogi Woreda. Bidders need a valid trade license, 2018 tax payment, VAT registration, and supplier registration certificate. Items must meet specifications and be delivered to the office.
Save Tender