Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline21 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO
  • opening dateጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale , Other Sales

በፍ/ባለመብት ማርታ አለማየሁ እና በፍ/ባለዕዳ እነ አስካለ ጉልማ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት ማርታ አለማየሁ እና በፍ/ባለዕዳ እነ አስካለ ጉልማ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 203306 በ11/7/2005 ዓ/ም እና መ/ቁ 26263 በ28/5/2005 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በኮ/ቀራኒዮ ከ/ከተማ ቀበሌ 01/05 የሚገኝ ቤ.ቁ 472 የቦታ ስፋት 318 ካ/ሜ የሆነ ይዞታው ደብተርያለው በመብት ፈጠራ ላይ በመመሪያው መሰረት መስተንግዶ የሚያገኝ ሆኖ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ 12,925,490.70 (አስራ ሁለት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃያ አምስት ሺህ አራት መቶ ዘጠና ብር ከ70/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +2512730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
A court-ordered auction sale of a 318 sq.m property (Block 472) in Kera Niyo sub-city, Kebele 01/05, held by the Federal Courts Execution Office. Bidders must deposit 1/4 of the starting estimate via CPO from the Commercial Bank of Ethiopia; the winner must pay the full amount within 15 days.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender