የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ጤና ጣቢያ የ2019 ዓ.ም የአንደኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ቋሚ የቢሮ ዕቃ፣ አላቂ የቢሮ ዕቃ፣ የፅዳት ዕቃ፣ የህትመት ውጤት፣ የደንብ ልብስ፣ የመድኃኒትና ሪኤጀንት፣ አላቂ የግንባታ ዕቃዎች እና የጉልበት ሥራ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የአንደኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ጤና ጣቢያ የ2019 ዓ.ም የአንደኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ቋሚ የቢሮ ዕቃ፣ አላቂ የቢሮ ዕቃ፣ የፅዳት ዕቃ፣ የህትመት ውጤት፣ የደንብ ልብስ፣ የመድኃኒትና ሪኤጀንት፣ አላቂ የግንባታ ዕቃዎች እና የጉልበት ሥራ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፡-
- በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑ ግብር ለመክፈላቸው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዘጋቢ የሆኑና የዚህን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ከሆነ ካደራጃቸው አካል አምራች ወይም በምርት ላይ እሴት የሚጨምሩ ከሆነ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመያዝ መግዛት ይችላሉ።
- ከታች የተጠቀሱትን ሎቶች የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
| የሎት ቁጥር | የሎት ዝርዝር | የተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ በኢት ብር (CPO) |
| ሎት 1 | ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች | 30,000 |
| ሎት 2 | አላቂ የቢሮ ዕቃዎች የጽሕፈት መሣሪያ | 20,000 |
| ሎት 3 | የፅዳት ዕቃዎች | 30,000 |
| ሎት 4 | የህትመት ውጤቶች | 23,000 |
| ሎት 5 | የደንብ ልብስ | 20,000 |
| ሎት 6 | መድኃኒትና ሪኤጀንት | 50,000 |
| ሎት 7 | አላቂ የግንባታ እቃዎች | 20,000 |
| ሎት 8 | የጉልበት ሥራ አገልግሎት | 10,000 |
- ተጫራቾች ጨረታ ሰነዱን ከተጋበዙበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በጤና ጣቢያው ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 410 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የእቃ ናሙና አይነት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- በተጫራች የሚሞላው የዋጋ ዝርዝር ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ተዘግቶ በቀጣዩ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በጤና ጣቢያው አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ አሟልተው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ዋጋ የለውም።
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወረዳ 10 ጤ/ጣቢያ ልዩ ቦታ ብሔረ ፅጌ ማርያም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ወረድ ብሎ
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- በ011 470 8031 ይደውሉ።
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ከተማ ወረዳ 10 ጤና ጣቢያ
✨ messages.ai_summary
Nifas Silk Lafto District 10 Health Station seeks suppliers for office furniture, consumable office supplies, cleaning materials, printed materials, uniforms, medicines and reagents, consumable construction materials, and labor services. Bidders must provide a renewed business license, supplier registration certificate, and VAT registration.
