የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የጭስ ማስወገጃ ሥርዓትን የማጽዳትና የጥገና አገልግሎት በሚያቀርቡ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ የስካይ ላይት ሆቴል የጭስ ማስወገጃ ስርዓትን የማፅዳትና የጥገና አገልግሎት በኮንትራት ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር RTCSSNT-T642
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የጭስ ማስወገጃ ሥርዓትን የማጽዳትና የጥገና አገልግሎት በሚያቀርቡ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ የስካይ ላይት ሆቴል የጭስ ማስወገጃ ስርዓትን የማፅዳትና የጥገና አገልግሎት በኮንትራት ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች፣ የዘመኑን የታደሰ ሀጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የታደሰ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከተፈቀደለት አካል በተጠቀሰው ምድብ ማቅረብ የሚችሉ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፥ ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ (PPPAA) የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-1642 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 70,000.00 / ሰባ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም ለ150 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል ማክሰኞ, መስከረም 19, 2019 ዓ.ም እስከ 08:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መከፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን 08:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር 044-547-8025
ኢ-ሜይል፡ KidistTa@ethiopianairlines.com
የተጫራቾች መንገዱ የተሳሳተ መሆኑን ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
