Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ ፖስታ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የተሽከርካሪ ጐማዎች እና፣ የመኪኖች ብራንዲንግ ቀለም ቅብ፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር የኢ/ፖ/አ/ድ ግጨ 03/2019 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ፖስታ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የተሽከርካሪ ጐማዎች እና፣ የመኪኖች ብራንዲንግ ቀለም ቅብ፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ በድርጅቱ ዋናው መሥሪያ ቤት ፋይናንስ ዲፖርትመንት 2ኛ ፎቅ የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር/ በየሎቱ በመከፈል ለጨረታው የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ግዥ ከፍል ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ግዥው እንደሚከተለው በሠንጠረዥ ተቀምጧል፡፡

ተ.ቁ ሎት የጨረታው አይነት በየሎቱ በሁኔታዎች ላይማስከበሪያ(CPO)
1 ሎት 01 የጽህፈት መሳሪያዎች 100,000.00
2 ሎት 02 የጽዳት ዕቃዎች 100,000.00
3 ሎት 03 የተሽከርካሪ መኪና ጐማዎች 100,000.00
4 ሎት 04 የመኪኖች ብራንዲንግ ቀለም ቅብ 100,000.00

ተጫራቶች በጨረታ ለመሳተፍ፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ
  2. ታክስ ክሊራንስ የታደሰ
  3. የቫት ሠርተፍኬት (የተጨማሪ እሴት ታክስ ሠርተፍኬት)
  4. የግብር ከፋይ ሠርተፍኬት (Tin certificate)
  5. ከሎት 1- 3 ለተዘረዘሩት የጨረታ አይነቶች የፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሠነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻው በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ናሙና ባላቀረቡበት እቃ ላይ ዋጋ መስጠት የለባቸውም ።
  6. ለመኪኖች ብራንዲንግ ቀለም የፋይናንሻል እና ቴከኒካል ሠነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻው በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ሌሎች በጨረታ ሠነዱ ላይ የተገለፁትን ሠነዶች አሟልተው ማቅረብ አለባቸው
  8. ተጫራቾች በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ በየሎቱ የ100,000.00(አንድ መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 9፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ፡፡
  11. ሲፒኦ /CPO/ ሲያሠሩ “የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት “Ethiopian postal Service enterprise” በማለት ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-11-73-00-62

የኢትዮጵያ ፖስታ

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Postal Service seeks suppliers for office supplies, cleaning materials, vehicle tires, and car branding paint via open tender across four lots. Bidders need a renewed business license, tax clearance, VAT and TIN certificates, and must submit samples; financial and technical documents required separately.
Save Tender