የባቱ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት አመት በስሩ ለሚተዳደሩ ባለበጀት መ/ቤቶች የተለያዩ 1ኛ አላቂ የጽህፈት መሣርያዎች፤ አላቂ የጽዳት እቃዎች 2ኛ የተለያዩ ህትመት ስራዎች 3ኛ የሰራተኛ ደንብ ልብስ የስፖርት ትጥቅ ና የተለያዩ የባህል ልብሶች፡፡
የባቱ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
የዕቃ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የባቱ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት አመት በስሩ ለሚተዳደሩ ባለበጀት መ/ቤቶች የተለያዩ 1ኛ አላቂ የጽህፈት መሣርያዎች፤ አላቂ የጽዳት እቃዎች 2ኛ የተለያዩ ህትመት ስራዎች 3ኛ የሰራተኛ ደንብ ልብስ የስፖርት ትጥቅ ና የተለያዩ የባህል ልብሶች፡፡ 4ኛ-ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች /ፋርኒቸሮች/ ና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፡-5ኛ-ሞተር ሳይክሎች የሞተር ሳይክል ጎማዎች የተለያዩ የመኪና ጎማዎችና የማሽነሪ ጎማዎች = በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በቀረበው የዋጋ ማቅራቢያ ፎረም በመሙላት እንድትወዳደሩ የተጋበዛችሁ ስለሆነ ያሸነፉበትን ዕቃ እስከ ባቱ ዝዋይ ከተማ ገንዘብ አስተዳደር /ጽ/ቤት ከተማ ድረስ የሚያቀርቡበትን የመጓጓዣ የማስጫኛ እና ማውራጃ ወጪውን በመጨመር ከዚህ በታች በተጠቀሰው መስፈርቶች የሚታሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።
- ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- በገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በሚጫረቱበት ዘርፍ የተመዘገቡ ስለመሆኑ ማስረጃ የሚያቀርብ፡፡
- ተጫራቾች የንግድ ስራ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብና የግብር ከፋይነት መለያ ና የቫት (VAT) ሰርትፍኬት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡:
- የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-11፡30 ሰዓት ድረስ የሚሸጥ መሆኑን፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ 500(አምስት መቶ ብር ብቻ) ለእያንዳንዱ ሰነድ በመከፈል ከመ/ቤታችን የግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ክፍል መግዛት የሚችሉ መሆኑን።
- ተጫራቾች ብር 30,000( ሰላሳ ሺህ) ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ ለጨረታ መስከበሪያ ሲፒኦ(CPO) ብቻ በባቱ ዝዋይ ከተማ ገ/አስተዳደር ጽ/ቤት ስም አስገብቶ ከጨረታ ሰነድ ፋይናል ሪሲት ኦሪጅናል ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ የዋጋ ሰነድ በጥራት ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመስሪያቤቱ ጥያቄ መስራት ብቻ በመሙላት በታሸገ ኤንቬሎፕ ሙሉ አድራሻውንና የተወዳደሩበትን ዕቃ አይነት 18/12/2018 ዓ.ም. እስከ 05/13/2018 ከሰዓት 8፡00 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ05/13/2018 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት/ባይገኙም በባቱ ከተማ ገ/አስተዳደር ጽ/ቤት ከሰዓት 8:30 ሰዓት የግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ክፍል ይከፈታል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ መንገድ ከገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብት በህግ የተጠበቀ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር /09-45-38-94-44/0911-51-02-44/ ደውለው ይጠይቁ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በበዓልና በዝግ ቀናት ላይ ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን ላይ ይሆናል፡፡
የባቱ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Procurement of office supplies, cleaning materials, printing services, staff uniforms, sports gear, cultural clothing, office furniture, electronics, motorcycles, and various tires for Bat Town Finance Office. Bidders must hold valid trade licenses, tax clearance, VAT registration, and be registered with the Ministry of Finance.
