Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 የአፄ ልብነድንግል ቅድመ እንደኛ፡ እንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት
  • Address Addis Ababa:Ethiopia, Phone: 0111552066
  • Website
  • Deadline02 Sep 2026, 5:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 200 /ሁለት መቶ ብር/
  • Bid Securityበጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ CPO እና የባንክ ዋስትና /bank guarantee/
  • opening dateበ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Categories Office Supplies And Services , Printing And Publishing , Textile, Garment & Leather

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ትምህርት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የእፄ ልብነ ድንግል ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያገለግሉ ግብዓቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 የአፄ ልብነድንግል ቅድመ እንደኛ፡ እንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ትምህርት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የእፄ ልብነ ድንግል ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያገለግሉ ግብዓቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህም መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊና ፍላጎት ያላችሁ አቅራቢዎች በየሎቱ ለተከፋፈሉ ዕቃዎች ከተራ ቁጥር ከ1-12 መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች ተጋብዘዋል።

  1. የመምህራን አስተዳደር ሰራተኞች የደንብ ልብስና የደንብ ልብስ ስፌት
  2. አላቂ የቢሮ እቃዎች
  3. የህትመት ስራዎች
  4. አላቂ የህክምና እቃዎች
  5. አላቂ የትምህርት እቃዎች
  6. አላቂ የጽዳት እቃዎች
  7. የጥገና እቃዎች
  8. የተለያዩ ማጣቀሻ መፅሐፍቶች
  9. የት/ቤቱ አጥር ስራ በእንጨትና በቆርቆሮ ሚስማር
  10. የመምህራን ማረፊያ አሮጌ ሶፋ ሙሉ እድሳት
  11. የሰራተኞች ከበብ ወይም ካፌ

ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈለ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው እንዲሁም ከሚያቀርቡት ዕቃ ወይም አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

  1. ማንኛውም ተጫራች የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ወይም በኤጀንሲው ድህረ ገፅ ላይ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው። የጨረታ ማስከበሪያ በተመለከተ፡-
ሎት 1. 28,000 / ሃያ ስምንት ሺህ ብር /
ሎት 2. 26,000 /ሃያ ስድስት ሺህ ብር/
ሎት 3. 3,000 /ሶስት ሺህ ብር /
ሎት 4. 2,000 /ሁለት ሺህ ብር /
ሎት 5. 8,000 /ስምንት ሺህ ብር /
ሎት 6. 28,396.28 / ሃያ ስምንት ሺህ ሶስት መቶ ዘጠና ስድስት ብር ከሃያ ስምንት ሳንቲም /
ሎት 7. 12,000 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/
ሎት 8. 6,000 /ስድስት ሺህ ብር/
ሎት 9. 20,000 / ሃያ ሺህ ብር/
ሎት 10. 2,000 /ሁለት ሺህ ብር/
ሎት 11. 2,000 /ሁለት ሺህ ብር/
ሎት 12. 26,452.80 /ሃያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሃምሳ ሁለት ብር ከሰማኒያ ሳንቲም/
  1. በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ CPO እና የባንክ ዋስትና /bank guarantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸው ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በላይ ለሆኑ ዕቃዎች የሚወዳደሩ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ለሚዘጋጀው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀናት በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ ማህተም ባረፈበት በታሸገ ኢንቨሎፕ በተዘጋጀው በጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በመምጣት ማስገባት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መዋዋል አለባቸው። በተጨማሪም ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በ15 ቀናት ውስጥ በአፄ ልብነ ድንግል ቅ/አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ንብረት ክፍል አጠናቀው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። ቢፈጠር ከፊት ለፊቱ ፊርማ ሊኖረው ይገባል። አለበለዚያ የተሞላው ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።
  6. የጨረታ ሰነዱ አንዱ የጨረታ መመሪያ መሆኑን ተጫራቾች ሊረዱት የሚገባ ሲሆን በጨረታ ሰነዱ ላይ ያልተካተቱ ችግሮች ቢገጥሙ በግዥ መመሪያ የሚዳኙ ይሆናል።
  7. ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ የሚከፈትበት ቀን በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1 ይከፈታል።
  8. የጨረታው መዝጊያና መከፈቻ ቀናት ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀናት ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን የጨረታው መከፈቻ እና መዝጊያ ቀናት ይሆናል።
  9. መስሪያ ቤቱ በግዥ ዝርዝር ከቀረበው የእቃ ብዛት ላይ 20% መቀነስና መጨመር መብት አለው።
  10. አሸናፊ ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ትምህርት ቤቱ ድረስ ያቀርባል።
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ የአሰራር ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. የጥቃቅንና አነስተኛ ላይ የተደራጁ ተጫራቾች ልዩ አስተያየት የሚደረገው በሚያመርቱት ምርት ብቻ ሆኖ ከተደራጁበት ተቋም በሚያቀርቡት ደብዳቤ ይሆናል።

አድራሻ፡- ቀጨኔ መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን ዝቅ ብሎ ከባህታዊ ገ/መስቀል ቤት ፊት ለፊት ወይም ከወረዳ 4 አስተዳደር ከፍ ብሎ የሚገኝ እፄ ልብነ ድንግል ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ነው።

ለበሰጠ መረጃ ስልክ ቁጥር:- 0111552062 / 0111267552 /

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ትምህርት ጽ/ቤት የአፄ ልብነ ድንግል ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for supplying school materials for the 2019 budget year, divided into 12 lots including office supplies, printing, uniforms, medical, cleaning, maintenance items, reference books, fence work, sofa renovation, and staff cafe. Bidders must have valid licenses and relevant registration.
Save Tender