በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በደቡብ ምእራብ ሸዋ ዞን የሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በደቡብ ምእራብ ሸዋ ዞን የሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
አንደኛ ዙር ለ2019 ዓ.ም የበጀት አመት በወረዳው ለሚገኙት መ/ቤቶች፡ የደንብ ልብሶች የጽዳት እቃዎች የጽህፈት መሳሪያዎች የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቋሚና አላቂ እቃዎችን ፤ የኤሌከትሮኒከስ እና ፈርኒቸሮች የመኪና እና የሞተር ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የተወዳዳሪዎች መስፈርት
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ግዴታ የተወጡ ስለመሆኑ የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተረሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ውስጥ የቀረቡትን ግዴታዎች አምነው መቀበል አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች በመንግስት ግዥ መሳተፍ እንደሚችል የሚገልጽ ከህጋዊ አካል የተሰጠ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የስራ ቀናት ውስጥ በእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ/ ብር በመከፈል ከሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛ የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ተጫራቾች በተገኙበት 4፡00 ሰአት ተዘግቶ በዛኑ ቀን 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የተወዳደሩበትን የእቃ ብዛት ተባዝቶ 2% በባንክ በተመሰከረ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ ብቻ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በፈለጉትና ማቅረብ በሚችሉት ዕቃዎች ላይ ብቻ መወዳደር ይችላሉ፡፡ አሸናፊ ተጫራች ተወዳዳሪ/ የውድድሩ ውጤት ከተነገረበት እስከ 7ኛ ቀን ቀርቦ ውል ካልፈረመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ይወረስበታል።
- ያሰቀመጥነው ብዛት እንደ አስፈላጊነቱ መጨመር እና መቀነስም ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ተወዳድረው ያሸነፉበትን ዕቃዎችን ሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት ያቀርባሉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ላይ ባይገኙም ጨረታውን መከፈት አያግድም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡ ከአዲስ አበባ በስተ ደቡብ ምዕራብ የምትገኘው ሰበታ ከተማ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር /0912245947/01133810035
የሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Open tender for the supply of uniforms, cleaning supplies, office equipment, electronics, furniture, and vehicle/motor tires to district offices. Bidders need a valid trade license, tax clearance, VAT registration, and supplier certification.
