ዳም ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የ2018 ዓ/ም ሂሳብ ዓመት የኦዲት ሪፖርት ብቃት ባለው የውጪ ኦዲተር ማሰራት ይፈልጋል፡፡
Dam Real Estate PLC
የ2018 ዓ/ም የሂሳብ ኦዲት አገልግሎት ጨረታ ማስታወቂያ
ዳም ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የ2018 ዓ/ም ሂሳብ ዓመት የኦዲት ሪፖርት ብቃት ባለው የውጪ ኦዲተር ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በሕግ የተፈቀደላቸውና ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ኦዲተሮች በጨረታው እንዲሳተፉ ጥሪ ያቀርባል።
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ለ2019 ዓ/ም ቅጂ፤
- የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ቅጂ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት ቅጂ፤
- የታደሰ የኦዲት ሙያ ፈቃድ/ሰርተፍኬት ቅጂ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት ቅጂ፤
- በኦዲት ሙያ የመሥራት ሕጋዊ ብቃትና ፈቃድ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ፤
- በተመሳሳይ የኦዲት ሥራ ላይ ያላቸውን የሥራ ልምድ የሚያረጋግጥ መረጃ(ካለ)፤
- የኦዲት ሥራውን ለማከናወን የሚችሉበትን የፋይናንስ እና የሥራ ማጠናቀቂያ ጊዜ ፕሮፖዛል ከዋጋ ጋር ማቅረብ።
ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት እና ከተጨማሪ እሴት ታክስ በኋላ ተብሎ በግልጽ ተለይቶ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
ተጫራቾች አስፈላጊ ሰነዶችን እና ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት አዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ሲኤምሲ ሚካኤል አካባቢ የሚገኘው የኢኮኖሚክስ አሶሴሽን ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 415 ከ18/12/2018 ዓ/ም እስከ 29/12/2018 ዓ/ም ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 10፡00 ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በ29/12/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 የሚዘጋ ሲሆን ዘግይቶ የሚገባ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
ለበለጠ መረጃ፦ 0923 08 09 00 / 0995 55 92 89
