በየካ ከ/ከተማ እንጦጦ ቁጥር አንድ ጤና ጣቢያ የሚከተሉትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በየካ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የእንጦጦ ቁጥር አንድ ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019
በየካ ከ/ከተማ እንጦጦ ቁጥር አንድ ጤና ጣቢያ የሚከተሉትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1. የሠራተኞች ደንብ ልብስ
- ሎት 2. የደንብ ልብስ ስፌት
- ሎት 3. ልዩ ልዩ የፅዳት ዕቃዎች ግዥ
- ሎት 4. አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 5. ቋሚ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 6. የህክምና መድሀኒቶች እና ሪጀንቶች ግዥ
- ሎት 7. የተለያዩ ጥገና ስራዎች
- ሎት 8. የህትመት ስራዎች
- ሎት 9. ለህንፃ፣ ለቁሳቁስና ለተገጣጣሚዎች ግዥ
- ሎት 10. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ጥገና ሥራዎች
በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በሙሉ የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፍቃድና የፌደራል ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት ዝርዝር መኖራቸውን ማረጋገጫ ደብዳቤ፣ የቫት ተመዝጋቢና ታክስ ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
- ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ በየሎቱ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል ከጤና ጣቢያው ፋይናንስ ክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ በየሎቱ የሚከተለውን መጠን መሆን አለበት፡፡
| ሎት 1. የሠራተኞች ደንብ ልብስ | ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) |
| ሎት 2. የደንብ ልብስ ስፌት | ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) |
| ሎት 3. ልዩ ልዩ የፅዳት እቃዎች ግዥ | ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) |
| ሎት 4. አላቂ የቢሮ እቃዎች | ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) |
| ሎት 5. ቋሚ የቢሮ እቃዎች | ብር 10,000.00 (አሥር ሺህ ብር) |
| ሎት 6. የህክምና መገልገያ ሪኤጀንቶች እና መድሀኒቶች | ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) |
| ሎት 7. የተለያዩ ጥገና ስራዎች | ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) |
| ሎት 8. የህትመት ስራዎች | ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) |
| ሎት 9. ለህንፃ፣ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች ግዥ | ብር 3,000.00 (ሦስት ሺህ ብር) |
| ሎት 10. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ስራዎች | ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) |
ከኦሪጅናል ጨረታ ሰነዳችሁ ጋር በፖስታ ውስጥ ተያይዞ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ እንደተመለከተው መሠረት ከነቫቱ በማሰብ በፖስታ በማሸግ ማህተም ባረፈበት ኦሪጂናል እና ኮፒ እሽግ ለያይቶ በማዘጋጀት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ ኮፒ የሌለው ኦሪጅናል ሰነድ ውድቅ ይሆናል።
- የጨረታው ውጤት እንደታወቀ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ የሚውለው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሲሆን በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ይታሸጋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በፋይናንስ ክፍል ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉበትን እቃ በራሳቸው ትራንስፖርት አጓጉዘው ጤና ጣቢያው ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሌላው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ መከፈቻ ቀን በፊት ባሉት የስራ ቀናት ውስጥ ለሚወዳደሩበት እቃ ናሙና ለሚቀርብባቸው በያይነቱ ናሙና ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ያልቀረበበት እቃ ዋጋ በሰነዱ ላይ ቢሞሉም ተቀባይነት የለውም፡፡
- ሎት 7 እና 10 ላይ የምትወዳደሩ ለጥገና የሚያስፈልገው እቃ በተወዳዳሪ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- ለአነስተኛ እና ጥቃቅን ተወዳዳሪዎች የተደራጃችሁበትን ዘርፍ የሚገልፅ የድጋፍ ደብዳቤ ማምጣት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻችን፦ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ልዩ ስሙ ቤሳ ወይም ጣሲያን ሌምባሲ ጎን የሚገኝ ሲሆን ለበለጠ መረጃ፤
እንጦጦ ቁጥር አንድ ጤና ጣቢያ ስልክ ቁጥር 0913 60 56 32 0913 66 67 47 099114 08 79
በየካ ክ/ከተማ እንጦጦ ቁጥር አንድ ጤና ጣቢያ
✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement of goods and services across 10 lots, including staff uniforms, tailoring, cleaning supplies, office items, medical drugs and reagents, maintenance, printing, building materials, and electronics repair. Bidders must hold a valid trade license, supplier registration, and VAT compliance.
