የ2018 በጀት ዓመት የሂሳብ ሰነዶችን በሕጋዊ እና በውጭ ኦዲተር አወዳድሮ ለማስመርመር
የኮንሶ ምሁራን ማህበር (Konso Intellectual Association)
የኦዲት ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
የኮንሶ ምሁራን ማህበር (Konso Intellectual Association) የ2018 በጀት ዓመት የሂሳብ ሰነዶቹን በሕጋዊ እና በውጭ ኦዲተር አወዳድሮ ለማስመርመር ይፈልጋል። በመሆኑም ሕጋዊ የኦዲት ድርጅቶች ባለሙያዎች በሚከተሉት መስፈርቶች መሠረት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች፦
- የንግድ ፈቃድ፦ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የኦዲት ሥራ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የምዝገባ ምስክር ወረቀት፦ ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ (AABE) የተሰጠ ሕጋዊ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ፦ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ።
- የሥራ ልምድ፦ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ማህበራትን ወይም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ኦዲት በማድረግ ረገድ በቂ የሥራ ልምድ ያላቸው እና ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ (ቅድሚያ ይሰጣል)።
የማመልከቻ አቀራረብ እና የጊዜ ገደብ፦
- ተጫራቾች የቴክኒክ እና የፋይናንሻል (የዋጋ) ማቅረቢያ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 6 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ሰነዳቸውን ማስገባት ይችላሉ።
- የማስረከቢያ ቦታ፦ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ጀርሜን አደባባይ አጠገብ ባለው የጉዲና ቱምሳ ሕንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401።
- ለበለጠ መረጃ በ 09 95 80 31 31 ይደውሉልን።
የኮንሶ ምሁራን ማህበር (Konso Intellectual Association)
✨ messages.ai_summary
The Konso Intellectual Association seeks a legally licensed audit firm to audit its 2018 budget year financial documents. Bidders must hold a renewed audit license, AABE registration, TIN/VAT certificates, and preferably experience auditing nonprofits or civil society organizations. Technical and financial proposals must be submitted in sealed envelopes.
Not stated in the notice: bid security, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
