Tender Detail

Tender Details

  • Company ራዕይ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
  • Address Addis Ababa Ethiopia, Phone: 0116734127
  • Website
  • Deadline24 Aug 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 500 አምስት መቶ ብር (የማይመለስ)
  • Bid SecurityበCPO ከላይ በተዘረዘሩት ሎቶች መሰረት ለእያንዳንዱ በተቀመጠው የብር መጠን መሰረት ወይም በጥሬ ገንዘብ
  • opening dateበዛኑ ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Categories Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather

የደንብ ልብስ፣ አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ የስፖርት መምህራን ትጥቅ፣ የመርብ ኳስ፣ የእግር ኳስ፣ የመምህራን ጋወን የጥበቃ እና የፅዳት የደንብ ልብስ የላብራቶሪ ወንበርና ጠርጴዛ፣ ኮንፒተር መግዛት

ራዕይ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት


የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2018 ዓ/ም

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

ራዕይ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የደንብ ልብስ አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ የስፖርት መምህራን ትጥቅ፣ የመርብ ኳስ፣ የእግር ኳስ፤ የመምህራን ጋወን የጥበቃ እና የፅዳት የደንብ ልብስ የላብራቶሪ ወንበርና ጠርጴዛ፣ ኮንፒተር መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. የደንብ ልብስ ሎት፡ ለጨረታ የሚያስይዙት የብር መጠን 15,180
  2. አላቂ የፅዳት እቃ ሎት 2 ለጨረታ የሚያስይዙት የብር መጠን 10,400
  3. አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች ሎት 3 ለጨረታ የሚያስይዙት የብር መጠን 6000
  4. አላቂ የቢሮ እቃዎች ሎት 4 ለጨረታ የሚያስይዙት የብር መጠን 4950
  5. አላቂ የትምህርት እቃ ሎት 5 ለጨረታ የሚያስይዙት የብር መጠን 10275
  6. ፕላንት ማሽነሪ መግዣ ሎት 6 ለጨረታ የሚያስይዙት የብር መጠን 7500
  7. ለህንፃና ቁሳቁስ መግዣ ሎትን ለጨረታ የሚያስይዙት የብር መጠን 5500

የተጠቀሰው የሥራ ዘርፍ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ መሆናቸውንና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ ተጫራቹ የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ በCPO ከላይ በተዘረዘሩት ሎቶች መሰረት ለእያንዳንዱ በተቀመጠው የብር መጠን መሰረት ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሚቀርበው አጠቃላይ ዋጋ ጋር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በተገለፀበት በ5 ቀን ውስጥ ውል መፈፀምና 1ዐ% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፣

ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ1ዐ ተከታታይ የሥራ ቀን ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታውን ሰነድ ከት/ቤቱ ሂሣብ ክፍል የማይመለስ ብር 500 አምስት መቶ ብር/ በመከፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች በተመረጠው ናሙና መሰረት በ7 ቀን ውስጥ እቃዎቹን ለት/ቤቱ እቃ ግምጃ ቤት ከፍል ሀላፊ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች ሠነዱ ላይ የተጠቀሱትን እቃዎች የሚሸጡበትን ዋጋና ሌሎች መረጃዎችን ተቋሙ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ በመሙላት ኦርጅናልና ኮፒ አድርገው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እስከ ሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሁሉም ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታከስ /VAT/ ያተካተተ መሆን አለበት።

ጨረታው የሚታሸገው በ11ኛው ቀን በ4፡ዐዐ ሰዓት ሲሆን በዛኑ ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾችና ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል ። ት/ቤቱ በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው፡፡

አድራሻ፡- ኮተቤ ኪዳነምህርት መውጫ 300 ሜትር ገባ ብሎ

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0116734127

ራዕይ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Procurement of uniforms, educational supplies, office items, cleaning materials, sports gear, laboratory furniture, and computers for Raey Primary School. Bidders need valid licenses, tax clearance, and VAT registration. Delivery within 7 days of sample selection.
Save Tender